Logo
News Photo

የኢኖቬሽንና ቴከኖሎጂ ሚኒስቴር ከአራት ዩኒቨርሲቲዎች ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ።

የኢኖቬሽንና ቴከኖሎጂ ሚኒስቴር ከጅማ፣ ድሬድዋ፣ከሐዋሳ እና ከደብረብርሃን ዩንቨርስቲዎች ጋር የምርምር፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር እና የኢኖቬሽን ተግባራትን በትብብር ለማከናወን የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል።

በዝግጅቱ ላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ዶ/ር በለጠ ሞላ ስምምነቱ  በኢኖቪዝ-ኬ ኢንኩቤሽን ማዕከል እና በዩኒቨርሲቲዎች ያሉ አቅሞችን አቀናጅቶ በመጠቀም በዘርፉ ውጤት ለማምጣ አላማ ያደረገ ነው ብለዋል።

የሚከናወኑ የምርምር፣ የኢኖቬሽን፣የቴክኖሎጂ ሽግግርና ስታርታፖችን የመደገፍ ብሎም ምቹ ስነ ምህዳር ከመፍጠር አንጻር ያሉ ስራዎችን በጋራ በመስራት ለሃገር ኢኮኖሚ እድገት ዘርፉ የሚጠበቅበትን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ያግዛል ብለዋል።

በፊርማ ስነ ስርአቱ ላይ የድሬደዋ ዩንቭርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም ስምምነቱ ዩንቨርስቲዎች የሰው ሃይል ልማት ስራቸውን በተቀናጀ መንገድ ለመስራት አስተዋጽኦ ይኖረዋል ብለዋል።

ዩንቨርስቲዎች ያላቸውን አቅም በሀገር ኢኮኖሚ ልማት ለማዋል በዚህ መልኩ ተባብሮ መስራት ፈጥኖ ውጤታማ ስራዎችን ለመስራት እንደሚያግዝ የተናገሩት የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጀማል አባ ፊጣ ናቸው።

በሃዋሳ ዩንቨርሲቲ የምርምር እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ታፈሰ ማትዮስ ዩንቨርስቲው በፍጠራ በምርምር እና በቴክኖሎጂ  ስራዎችን ለመስራት ያለውን ከፍተኛ ፍላጎት ጠቅሰው ይህን መሰል ቅንጅት መፈጠሩ ያሉ አቅሞች እንዳይባክኑ ያደርጋል ብለዋል።

የደብረብርሃን ዩንቨርሲቲ የምርምር እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር አዝመራው አየሁ ዩንቭርሲቲው ከሚኒስቴሩ ጋር በርካቲ ውጤታማ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ጠቅሰው ይህ ስምምነት የነበሩ ሰራዎችን ከማጠናከር ባለፈ ዩንቨሪሲቲው አቅሙን እንዲጠቀም ያግዘዋል።

ከስትራይድ ኢትዮጵያ 2016 ኤክስፖ (STRIDE Ethiopia 2024 Expo) ጎን ለጎን በዘርፉ ርእሰ ጉዳዬች ላይ ከሙህራን፣ከአጋር የልማት ድርጅቶች፣ከፈጠራ ባለሞያዎችና የግሉ ዘርፍ አንቀሳቃሾች ጋር ዘርፉን ለማጠናከር የሚረዱ ግብአቶችን ለማሰባሰብ ያለሙ ውይይቶች እየተካሄዱ ይገኛሉ።

Share This News

Comment