Logo
News Photo

የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ የቦርድ አመራሮች ከዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ጋር ውይይት አካሄዱ።

የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ የቦርድ ሊቀመንበር የሆኑትና በጠቅላይ ሚኒስቴር ፅ/ቤት የዲሞክራሲ ማዕከል ግንባታ ሚኒስትር የተከበሩ አቶ ዛዲግ አብርሃና የቦርድ አመራሮች ከዩኒቨርሲቲው መምህራን፣ የአስተዳደር ሠራተኞች እና የተማሪዎች ህብረት ጋር የተወያዩ ሲሆን ቦርዱ ከሠራተኞች ጥቅማጥቅም መከበር፣ ከትራንስፖርት ችግር እና ከመኖሪያ ቤት ጋር ተያይዘው የሚነሱ ችግሮች በአፋጣኝ እንዲፈቱ የበኩሉን ድጋፍ እንዲያደርግ ጥያቂያቸውን አቅርበዋል፡፡

የቦርድ ሊቀመንበሩ ክቡር አቶ ዛዲግ አብርሃ በበኩላቸው ቦርዱ ከዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራርና ማኔጅመንት ጋር በመሆን ችግሩን በአጭር፣ በመካከለኞ እና በረጅም ጊዜ ለመፍታት አስፈላጊውን ሁሉ ጥረት ያደርጋል ብለዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ማህብረሰብም በበኩላቸው በዩኒቨርሲቲው ሁለንተናዊ ለውጥ እንዲመጣ ስራቸውን በባለቤትነት በመከወን የበኩላቸውን መወጣት አለባቸው ሲሉ አስገንዝበዋል፡

Share This News

Comment