Logo
News Photo

ዓለም አካባቢ ቀን በዓልን አስመልክቶ “መሬታችን ለነጋችን”

የዓለም አካባቢ ቀን በዓልን አስመልክቶ “መሬታችን ለነጋችን” “የመሬት ማገገም፣ በረሃማነትና ድርቅን መቋቋም” በሚል መሪ ቃል በአለም አቀፍ ደረጃ ለ51ኛ ጊዜ፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ31ኛ ጊዜ የአለም የአካባቢ ቀን በዓል የድሬዳዋ አስተዳደር የአካባቢ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ባለስልጣን ሰራተኞች ፣የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የጂኦግራፊና አካባቢ ጥናት ትምህርት ክፍል ተማሪዎችና መምህራኖች እንዲሁም  የሐርላ ቀበሌ ነዋሪዎችና ተማሪዎች እና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በአስተዳደሩ ሀርላ የገጠር ቀበሌ የተተከሉ ችግኞችን በመንከባከብ ፣ ዉሀ በማጠጣት እና ግንዛቤ በመፍጠር  ተከብሯል፡፡

 በስነ ስርዓቱ ላይ የባለስልጣን መ/ቤቱ ሃላፊ አቶ አብዱ መሀመድ እለቱን አስመልክቶ መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን መሬት እንዲያገግም በማድረግ በረሃማነትና ድርቅን በመቋቋም የተራቆቱ ቦታዎችን በማልማት ከተረጂነት መላቀቅ እና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር አካባቢን መንከባከብ እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል፡፡

በተጨማሪም የምግብ ዋስትናን ለማረገጋጥ የሚቻለው ለአከባቢያችን ጥበቃና እንክብካቤ ሲደረግለት እንደሆነ ተመላክቷል።

በሌላ በኩል ድሬዳዋ በተደጋጋሚ የሚጋጥማትን የጎርፍ አደጋ ስጋትን ለመከላከል ለአካባቢ ጥበቃ ትኩረት መስጠት ያስፈልጋል ተብሏል፡፡

Share This News

Comment