Logo
News Photo

ቱር- ድሬ የቱሪስት ጠቋሚ መተግበሪያ

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ቱር- ድሬ የሚል ስያሜ የተሰጠውን  የቱሪስት መረጃ የሞባይል መተግበሪያ በማበልፀግ ለአስተዳደሩ ባህልና ቱሪዝም ፅ/ቤት አስረከበ፡፡

በዚሁ ፕሮግራም ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ ባህልና ቱሪዝም ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሚኪያስ እንዳለ ቱር-ድሬ የሞባይል መግበሪያ የድሬዳዋን የቱሪዝም እንቅስቃሴ ለማሳድ ትልቅ እገዛ የሚያደርግ ነው፡፡

በተመሳሳይ በዩኒቨርሲቲው የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የምርምርና ማኅበረሰቡ ፅ/ቤት ኃላፊ ዶ/ር ግርማ ቤካ ዩኒቨርሲቲው ከዚህ ቀደም በአስተዳደሩ የሚሠሩ ልማት ሥራዎችን በዘመነ መልኩ የሚያፋጥኑ ተግባራትን ሲፈፅም መቆየቱን አውስተው በቀጣይም እነዚህ ተግባራት ተጠናክረው የሚቀጥሉ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ቱር-ድሬ የቱሪስት ጠቋሚ የሞባል መተግበሪያ በድሬዳዋ የሚገኙ የቱሪስት መዳረሻዎችን ፣ ሆቴሎችን ፣ ሆስፒታሎችን እና ..ወዘተ የሚገኙበትን ስፍራ የሚጠቁም የሞባል መተግበሪያ መሆኑን በፕሮግራሙ ላይ ተገልፃል፡፡

Share This News

Comment