Logo
News Photo

በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የስራ ፈጠራ ስልጠና ሲወስዱ የነበሩ ሰልጣኞች ተመረቁ፡፡

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስ እና ቴክሎጂ ኢንኩቤሽን ማዕከል ከኦርቢት ኢኖቬሽን ሃብ ጋር በመተባበር ለአራት ወራት በስራ እድል ፈጠራ ፅንሰሃሳቦች ላይ ስልጠና ወስደው ያጠናቀቁ ሰልጣኞችን አስመርቋል፡፡ በምረቃ ፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚደንት ዶ/ር ኡባህ አደም ሰልጣኞችን እንኳን ደስ አላችሁ ካሏቸው በኋላ በቀጣይነት ወደቢዝነስ አለም ለሚያደርጉት ጉዞ በትዕግስት እና በጽናት የሚያጋጥማቸውን ተግዳሮቶች በማለፍ ውጤታማ ሊሆኑ እንደሚገባቸው አሳስበዋል፡፡ ስልጠናውን ያጠናቀቁት ስምንት ስታርታፖች ሲሆኑ እያንዳንዱ በስራቸው ሁለት እና ከዚያ በላይ አባላት ያላቸው ናቸው፡፡

በቀጣይነትም ኦርቢት ኢኖቬሽን ሃብ ከማስተርካርድ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር ያዘጋጀላቸውን የሁለት ሺህ ዶላር ሽልማት የሚያገኙ ሲሆን ወደንግዱም አለም የሚቀላቀሉ ይሆናል፡፡ 

በምረቃ ፕሮግራሙ ላይ ከኦርቢት ኢኖቬሽን ሃብ፣ የኢትዮጲያ ልማት ኢንስቲትዩት፣ ከድሬዳዋ አስተዳደር የሚመለከታቸው ቢሮዎች የተወከሉ እንዲሁም የዩኒቨርሲቲው ዲኖች እና ዳይሬክተሮች ተካፍለዋል፡፡

Share This News

Comment