ለመዉጫ ፈተና አስፈፃሚዎች ፈተና አሰጣጥ ዙሪያ ገለፃ ተደርገ
ከሰኔ 14 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ ለሚሰጠው ሀገር አቀፍ የመዉጫ ፈተና ለመፈተን ከሐረማያ ዩኒቨርሲቲ፣ ከጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ፣ ከአርሲ ዩኒቨርሲቲ እና ከኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ወደ ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ለተመደቡት ፈታኝ መምህራን እንዲሁም ለግቢ ፀጥታ ሀይል አባላት ስለ ፈተና አሰጣጥ ዙሪያ ከትምህርት ሚኒስቴር ፈተናውን እንዲያስተባብሩ በተመደቡ አቶ ፈቀደ በኩል አስፈላጊው ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡
የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ጉዳዩች ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር መገርሳ ቃሲም እንዲሁም የአስተዳደርና ልማት ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሰለሞን ዘሪሁን በፕሮግራሙ ላይ በመገኘት ለፈታኞች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት በማስተላለፍ ከቤቱ ለተነሱ ጥያቄዎች አስፈላጊውን ማብራሪያ በመስጠት ቆይታቸው ያማረ እንዲሆን ተመኝተዋል፡፡
በመጨረሻም ፈተናውን ለመስጠት የሚያስችል ሁሉም ዝግጅት መደረጉ ተገልጿል።
Share This News