Logo
News Photo

በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ መምህራንና ተመራማሪዎች የተፃፉ አራት መጽሐፍ ተመርቀው ለንባብ በቁ።

ሀገር በቀል ዕውቀት ላይ ጥናትና ምርምር ሲደረግባቸው የነበሩ የምርምር ሥራዎች ወደ መፅሐፍ እንዲቀየሩ በተሰጠው አቅጣጫ መሰረት አራት መፅሐፎች በዛሬው እለት ተመርቀው ለንባብ በቅተዋል፡፡

ለምረቃ የበቁት አራት መፅሀፎች በመምህር ዳንኤል መንግሰቴ ሁለት መጽሀፍት ''Into the Life of Harari People: Literature and Their Epic Proverbs እና ''Immortal as a Soul: Toward Issa Oral Lyric Poetry and Their Functions'' ፣ በመምህር ሰብስቤ ጌታሁን በኦሮምኛ ቋንቋ ሸጎዬ (shaggooyyee) እንዲሁም በረ/ፕሮፌሰር ንጉስ ገ/መድህን ''Indigenous Rangeland Management System By Pastoral Communities of Dire Dawa Administration'' የተሰኙት መፅሐፍት ናቸው፡፡

በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የዩኒቨርሲቲው የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ተማም አወል በሀገር በቀል ዕዉቀቶች ላይ መሠረት አድርገው የሚጻፉ መፅሐፍት የአንድን ማህበረሰብ ታሪክ፣ ባህል እና የአኗኗር ዘዬን ለትዉልድ ሰንደን ለማስተላለፍ ሁነኛ መንገድ መሆኑን ጠቅሰው በዚህ ረገድ መፅሐፎቹ ታትመው ለንባብ መብቃታቸው አስተዋጽኦው የጎላ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

ዶ/ር ተማም አያይዘውም እንደተናገሩት በዩኒቨርሲቲው የተመረቁትን መጽሀፍት ሙሉ የህትመት ወጪያቸውን እንደሸፈነ ገልጸው በቀጣይም በዩኒቨርሲቲው መምህራን የሚሠሩ የምርምር ሥራዎች አስፈላጊው ሙያዊ ግምገማ ተደርጎባቸው ለንባብ እንዲደርሱ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ቃል ገብተዋል፡፡

ከመፅሐፍ ምረቃው ጎን ለጎንም በዩኒቨርሲቲው ድጋፍ ''Magnitude and Associated Factors On Harmful Traditional Practices Among Children in Dire Dawa Administration, Eastern Ethiopia'' በሚል ርዕስ በረ/ፕሮፌሰር አለሙ ጉታ እና የጥናት ባልደረቦቹ የተሰራው የምርምር ውጤት ለታዳሚያን ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

Share This News

Comment