Logo
News Photo

በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ሲሰጥ የነበረ ሃገር አቀፍ የመውጫ ፈተና በስኬት ተጠናቀቀ።

ከሰኔ 14 - 19/2016 ዓ/ም ለተከታታይ ስድስት ቀናት ለመጀመርያ ዲግሪ ተመራቂ ተማሪዎች የተሰጠ ሲሆን የመውጫ ፈተና አሰጣጥ ሂደቱ ያለ ምንም ችግር መጠናቀቁን ለማወቅ ተችሏል። የዩኒቨርስቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶ/ር መገርሳ ቃሲም እንደገለጹት በዘንድሮ የሃገር አቀፍ የመውጫ ፈተና በተሳካ መልኩ ለመስጠት የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ዩኒቨርሲቲው ማከናወኑ ፈተናው ያለ ችግር መካሄዱ ማሳያ ነው ብለዋል። 

በስተመጨረሻም ዶ/ር መገርሳ እንደገለፁት በመውጫ ፈተና አሰጣጥ ሂደት በስኬት እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ለነበራቸው ICT ቡድን፣ ከተለያየ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ ፈታኝ መምህራን፣ በአጠቃላይ የትምህርት ሚኒስቴር ቡድን፣ የፀጥታ ሀይል፣ የፈተና ግብረ ሀይል እና የፈተና አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት ምስጋናቸውን አቅርበው ለተፈታኝ ተማሪዎች መልካም እድል ተመኝተዋል።

Share This News

Comment