ዩኒቨርሲቲው ተልዕኮዎቹን ከማሳካት አንፃር አበረታች ውጤት እያሰመዘገበ መሆኑን ዶ/ር ኡባህ አደም ገለጹ፡፡
በዛሬው ምረቃ ስነ-ስርዓት ላይ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም እንደተናገሩት ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ሀገራዊ ተልእኮ ተሰቷቸው ከተቋቋሙት 15 የአፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲተዎች አንዱ ነው፡፡
እነዚህን ተልዕኮዎች ከማሳካት አንፃር ዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ እንቅስቃሴ ሲያደርግ መቆየቱን ጠቁመው በተለይም ሀገራችን የምትፈልገውን የሰለጠነ የሰው ኃይል በጥራት ከማቅረብ በተጨማሪ ማኅበረሰባዊ እድገት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ችግር ፈቺ ምርምሮችን በማከናወን እና የአካባቢውን ማኅበረሰብ ባሰተፈ መልኩ የተለያዩ አገልግሎቶችን በመስጥ አበረታች ውጤት ማስመዝገቡን ገልፀዋል፡፡
በተለይም የትምህርት ተደራሽነትን ከማስፋት አንጻር በአሁኑ ሰዓት ከ14 ሺህ በላይ ተማሪዎችን በመጀመሪያ ዲግሪ በ51 የትምህርት ፕሮግራሞችን 1 ሺህ 71 በሁለተኛ ዲግሪ በ48 የትምህርት ፕሮግራሞች በመደበኛና በኢ-መደበኛ በድምሩ 15 ሺህ 8 መቶ ተማሪዎችን በማስተማር ላይ ይገኛል፡፡
የትምህርት ፍታዊነትን ከማረጋገጥ አንፃርም በበጀት ዓመቱ በተሠራው ሥራ የኢኮኖሚ ድጋፍ ለሚሹ በተለይም ለሴት ተማሪዎች የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ ለአካባቢው ማኅበረሰብም 83 ተማሪዎች በመጀመሪያ ዲግሪ 44 ተማሪዎች በሁለተኛ ዲግሪ ነፃ የትምህርት ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ አድርጓል፡፡
የትምህርት ጥራትን ከማረጋገጥ አንፃርም በበጀት ዓመቱ በመምህራን ልማት ፕሮራም 166 መምህራንን ለሁለተኛ ዲግሪ ፣177 መምህራንን ለሦስተኛ ዲግሪ ፣17 መምህራንን በስፔሻሊቲና ሰብ-ስፔሻሊቲ በድምሩ 360 መምህራን በውጪ አገርና በአገር ውስጥ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ እንደሚገኙ ጠቁመዋል፡፡
በአሁኑ ሰዓትም በሥራ ላይ ያሉ መምህራን በትምህርት ደረጃ ስብጥር የመጀመሪያ ዲግሪ 7.6 በመቶ ፣ ሁለተኛ ዲግሪ 81 በመቶ እና ሦስተኛ ዲግሪ 8 በመቶ ማድረስ ተችሏል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ የተግባር ተኮር ትምህርቶችን ለማጠናከር የቤተ-ሙከራ ወርክሾፕን ለማደራጀት አስፈላጊውን በጀት በመመደብ ግብዓቶችን የማሟላት ሥራ የተሠራ ሲሆን የትምህርት አግባብንትን ለማሻሻል በተሠሩት ሥዎችም በተሠራው ሥራ ከ8 መቶ በላይ ተማሪዎች የተለያዩ የሰራ ቅጥርና የሥራ ፈጠራ ክህሎት የተሠጣቸው መሆኑን ዶ/ር ኡባህ በንግግራቸው አብራርዋል፡፡
በዚሁ የምረቃ ስነ-ስርዓት ላይ የተገኙት የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የቦርድ አባልና የኢስት አፍሪካ ሆልዲንግ ኩባኒያ የቦርድ ሊቀመንበር ክብር አቶ ብዙአየሁ ታደለ ተመራቂ ተማሪዎች ሀገራችሁ ከእናንተ የምትጠብቀውን እገዛ ለመወጣት ሥራ ፈጣሪ በመሆን በምትሠማሩበት መስክ ሁሉ ስኬታማ ለመሆን ከወዲሁ ዝግጅት ልታድርጉ ይገባል ብለዋል፡፡
Share This News