Logo
News Photo

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የማስተማሪያና ሪፈራል ሆስፒቲል የ2016 ዓ.ም የክረምት በጎፈቃድ አገልግሎት መርሀግብርን ዛሬ አስጀመረ፡፡ የበጎፈቃድ አገልግሎት መርሀግብሩ በይፋ ያስጀመሩት የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም ዩኒቨርሲቲው በዘንድሮው የ2016 ዓ.ም የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የተለያዩ ተግባራትን ያከናውናል፡፡

በዋነኝነትም የጤና ምርመራና የጤና ግንዛቤ ማስጨበጫ አገልግሎት ፣ደም ልገሳ፣ ወላጅና አሳዳጊዎቻቸው ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ህጻናት ተማሪዎች፣ እንዲሁም የተለያዩ የትምህርት መርጃ ቁሳቁስ ድጋፍ ፣ በአረጋዊያን ማዕከላት ለሚገኙ አረጋዊያን እንክብካቤና ድጋፍ ፣ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሀ ግብር የችግኝ ተከላ እንዲሁም ለተመረጡ አቅመ ደካማ የኅብረተሰብ ክፍሎች የቤት እድሳት እንደሚደረግ አብራርተዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው መምህራንና ተማሪዎችም በርካታ ወገኖችን ተጠቃሚ ለማድረግ በሚሠራው የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግልት ላይ ንቁ ታሰትፎ በማድረግ የበኩላቸውን ይወጡ ዘንድ ዶ/ር ኡባህ በዚሁ ወቅት ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡ 

በተመሳሳይ በዩኒቨርሲቲው የህክምና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዲን እንዲሁም የሆስፒታሉ ተጠባባቂ ቺፍ ኤክስኩቲቭ ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ሁሴን መሐመድ እንዳሳወቁት ከሐምሌ 27 ቀን እስከ ጳጉሜ 5 ቀን 2016 ዓ.ም በሚዘልቀው የዘንድሮው የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በማስተማሪያና ሪፈራል ሆስፒታል ለ12 ሺህ ማህበረስብ አገልግልት ለመስጠት ዝግጅት የተደረገ መሆኑን አሳውቀው በዚሁ መርሀ ግብር በዋነኝነት የጤና ምርመራና ጤናን አስመልክቶ ግንዛቤ ማስጨበጫ  ትምህርት እንደሚሰጥ ዶ/ር ሁሴን ገልፀዋል፡፡


Share This News

Comment