Logo
News Photo

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የ2016 በጀት ዓመት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ አካሄደ

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ማኔጅመንት ካውንስል በዩኒቨርሲቲው የሚገኙትን የአካዳሚክ ጉዳዩች ምክትል ፕሬዝዳንት፣ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት፣ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዝዳንት፣ የአስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት እና የማስተማሪያና ሪፈራል ሆስፒታልን የ2016 በጀት ዓመት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ አካሂዷል፡፡

በግምገማው ላይ በ2016 በጀት ዓመት የዩኒቨርሲቲውን ተልእኮ እና የትኩረት መስክ መሰረት ባደረገ መልኩ አምስቱ ዋና ዋና ዘርፎች በመማር ማስተማር፣ በጥናትና ምርምር እንዲሁም በማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎቶችን የነበራቸውን አፈፃፀም ለማኔጅመንት ካውንስሉ ያቀረቡ ሲሆን አጠቃላይ በተገኙ ውጤቶችና ቀጣይ ስራዎች ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡

ለአብነትም በይነ መረብን በመጠቀም የተከናወኑ የመማር ማስተማር ስራዎች፣ ከአጋር አካላት ጋር የተሰሩ የምርምርና ቴክኖሎጂ ስራዎችና ችግር ፈቺ ማህበረሰብ አቀፍ ተግባራት አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ በተጨማሪም የማስተማሪያና ሪፈራል ሆስፒታል በከፊልም አገልግሎት መስጠት እንዲጀምር በማድረግ ህብረተሰቡ የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ መደረጉ በቀጣይ በተሟላ ሁኔታ አገልግሎቱን ለማስፋት ጠቃሚ ልምድ የተገኘበት መሆኑ ተገልጿል፡፡


Share This News

Comment