በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በፕሮግራሞች ደረጃ የኢንዱስትሪዎች ማፒንግ ሴሚናር ተካሄደ
በኢንዱትሪ ትስስር እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት “Industry needs assessment result: Staff Engagement in Addressing Industry Challenges” በሚል ርእስ የዩኒቨርሲቲው መምህራን እና ተመራማሪዎች፣ኮሌጅ ዲኖች፣ ዳይሬክተሮች እና ሌሎች የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ በተገኙበት የግማሽ ቀን ሴሚናር ተካሂዷል፡፡ ሴሚናሩ ያተኮረው የኢንዱስትሪዎችን የስልጠና፣ የማማከር፣ የቴክኖሎጂ እና ሌሎች ተያያዥ ፍላጎቶች ዳሰሳ ጥናት ውጤት ሰነድ ላይ ያተኮረ ሲሆን ኮሌጆች፣ ትምህርት ክፍሎች እና ሌሎች የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ የኢንዱሰትሪውን ፍላጎት እንዲገነዘቡ እና በቀጣይ በኢንተርንሺፕ፣ ኤክስተርንሺፕ፣ በምርምር፣ በማማከር እና ቴክኖሎጂ ሽግግር የሚሰሩ ስራዎች የኢንዱሰትሪውን ፍላጎት ማእከል ያደረገ እንዲሆን ለማድረግ ከኢንዱስትሪዎች ጋር የሚደረጉ የትስስር ስራዎችን ለማጠናከር ያለመ ነው፡፡ በቀጣይነትም ከሴሚናሩ የተገኘው ግብአት ቀምሮ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከኢንዱስትሪዎች ጋር በመወያየት የጋራ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እንደሚሰራ
Share This News