Logo
News Photo

የስታርትአፕ10 ፕሮጀክት የፍጻሜ ውድድር በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ተካሄደ።

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስና ቴክኖሎጂ ማበልጸጊያ ማዕከል CIHEAM Bari ከተባለው የጣሊያን ኢንቲትዩት ጋር በመተባበር ሲያካሂድ የነበረው የStartup10 ፕሮጀክት የፍጻሜ ውድድር በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ተካሄደ። 

በፍጻሜ ውድድሩ ላይ በፕሮጀክቱ ታቅፈው አስፈላጊውን የኮቺንግ እና በዩኒቨርሲቲውና በአለም አቀፍ ባለሙያዎች  ልዩ ልዩ ድጋፍ ሲደረግላቸው የነበሩ የቢዝነስ ባለቤቶች ስራዎቻቸውን ለዳኞች ያቀረቡ ሲሆን በቀጣይ የውድድሩ አሸናፊ የሚሆነው ቢዝነስ ጣሊያን ሀገር በመሄድ ስራዎቹን የሚያቀርብና በሀገሪቱ ከሚገኙ ድርጅቶች ጋር አብሮ የመስራት እድል የሚመቻችለት ይሆናል። ከዚህ በተጨማሪም የውድድሩ አሸናፊ የሚሆነው ቢዝነስ የ5000.00 Euro የገንዘብ ድጋፍ እንደሚደረግለት በፕሮጀክቱ አስተባባሪዎች ገለጻ ተደርጓል። 

ይህ ፕሮጀክት በሜዲትራንያንና በአፍሪካ ውስጥ በሚገኙ በተመረጡ አስር ሀገራት ማለትም በአልጄሪያ፣ አልባኒያ፣ ቦሲንያና ሄርዞጎቭኒያ፣ ግብጽ፣ ኢትዮጵያ፣ ጆርዳን፣ ኬንያ፣ ሊባኖስ፣ ቱኒዝያና ኡጋንዳ ውስጥ በሚገኙ 22 ኢንኩቤሽን ማዕከላት ውስጥ ለአንድ አመት ሲተገበር የቆየ ሲሆን ፕሮጀክቱ በሀገራችን ኢትዮጵያ በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስና ቴክኖሎጂ ማበልጸጊያ ማዕከል እንዲሁም በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ  ኢንኩቤሽን ማዕከል ውስጥ ሲተገበር የቆየ ሲሆን ዋና አላማውም በምግብ ዋስትናና በወጣቶች የስራ ፈጠራ ላይ ትኩረት አድርገው የሚሰሩ ቢዝነሶችን በአቅምና በገንዘብ መደገፍ ሲሆን አጠቃላይ ፕሮጀክቱ በጣልያን የውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤትና በጣልያን መንግስት አለም አቀፍ ትብብር (MAECI) የገንዘብ ድጋፍ ሲደረግለት እንደነበረ ለመረዳት ችለናል።

Share This News

Comment