Logo
News Photo

ለድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ሲሰጥ የነበረው የETW ስልጠና ተጠናቀቀ።

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስና ቴክኖሎጂ ማበልጸጊያ ማዕከል (DDU-BTIC) ከኢትዮጲያ ኢንተርፕረነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ለዩኒቨርሲቲያችን መምህራን በሁለት ዙር ሲሰጥ የነበረው የETW (Entrepreneurial Training Workshop) ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡ 

ይህ ስልጠና አለምአቀፍ ደረጃውን የጠበቀና ተግባር ተኮር ስልጠና ሲሆን ስልጠናውን ከኢትዮጲያ ኢንተርፕረነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት  በመጡ ስድስት የተመሰከረላቸው (Certified) አሰልጣኞች ተሰጥቷል። 

በዚህ በሁለት ዙር ለተከታታይ 15 ቀናት ሲሰጥ የቆየውን ስልጠና 33 ወንድ እንዲሁም 4 ሴት በአጠቃላይ 37 መምህራን ስልጠናውን በተቀመጠው መስፈርት መሰረት በብቃት በማጠናቀቃቸው የእውቅና የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል፡፡ 

በዩኒቨርሲቲያችን በሁለት ዙር ሲሰጥ የቆየውን ስልጠና የተከታተሉ ሰልጣኝ መምህራን በአለም ደረጃ 904ኛ እና 905ኛ ዙር ሰልጣኞች ሲሆኑ በቀጣይ ለተመረጡ ሰልጣኞች የአሰልጣኞች ስልጠና (Training for Trainers) የሚሰጣቸው መሆኑን ከስልጠናው አስተባባሪዎች ለመረዳት ችለናል።

Share This News

Comment