ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ገበያ ከተሰኘ ድርጅት ጋር በመተባበር ተማሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የሳፋሪኮም የታለንት ክላውድ ፕሮግራም ተጀመረ::
ተማሪዎችን ደረጃቸውን የጠበቁ የኦንላይን ኮርሶች እንዲያገኙ እድል የሚከፍት እንደሆነ የተነገረለት የሳፋሪኮም ታለንት ክላውድ ፕሮግራም በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ተጀምሯል፡፡ ፕሮግራሙ የኦንላይን ኮርሶችን ለመውሰድ ፍላጎት ላላቸው ተማሪዎች በሙሉ የተዘጋጀ ሲሆን በፕሮግራሙ በኢኮኖሚ የተጎዱ ሴቶች፣ አካል ጉዳተኞች ፣ እንዲሁም ተፈናቃዮች ነፃ እድል የሚያገኙ ሲሆን ፍላጎቱ ላላቸው ተማሪዎች ደረጃቸውን የጠበቁ አለማቀፋዊነት ይዘት ያላቸው የኦንላይን ኮርሶችን የተዘጋጁ እና ክህሎታቸውን እንዲያሳድጉ የሚረዳ እድል እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡
በማስጀመሪያ ፕሮግራሙ ከሁሉም ኮሌጆች የተውጣጡ ተማሪዎች፣ የዩኒቨርሲቲው አመራሮች እንዲሁም ከሳፋሪኮም፣ ገበያ እንዲሁም ከጃይካ ግብረሰናይ ድርጅት የተወከሉ እንግዶች ታድመውበታል፡፡
Share This News