Logo
News Photo

የአፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ በጋራ በመሆን በአንድ ማኅበር ስር መንቀሳቀሳቸው ርዕያቸውንና ተልዕኮዋቸውን ከማሳካት ባለፈ ሀገር የያዘችውን የእድገትና የብልፅግና ጉዞ ለማሳካት ትልቅ ፋይዳ እንደሚኖረው ተገለፀ፡፡

በዛሬው እለት በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በመካሄድ ላይ የሚገኘውን የአፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲዎች ኮንሰርተየም የምሥረታ ፎረምን በንግግር የከፈቱት በኢፌዲሪ የትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዲዔታ ክቡር አቶ ኮራ ቱሹሜ እንዳሉት ዩኒቨርሲቲዎች በጋራ በአንድ ፎረም ስር ሆነው መንቀሳሰቀሳቸው ዘርፈ ብዙ ጥቅም ያስገኝላቸዋል፡፡

በተለይም በአሁኑ ሰዓት ሀገራችን የያዘችውን የዕድግት ጉዞ ከዳር ለማድረስ የአፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲዎች የሚኖራቸው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ሚኒስቴር መስሪያቤቱ በሚያወጣቸው ፖሊሲዎች ዩኒቨርሲቲዎች ትልቅ ድርሻ እንዲኖራቸው እንዲሁም በጋራ ሀብትን የመጠቀም ፣ በጋራ የምርምር ሥራዎችን በመፈፀም የተሰጣቸውን ሀገራዊ ተልዕኮ ከማሳካት አንፃርም በጋራ መንቀሳሰቀሳቸው ትልቅ አቅም እንደሚፈጥርላቸው በመግለጽ በፎረሙ ቆይታቸው የተሳካ እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡ 

በዚሁ ፎረም የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም በተመሳሳይ የትኩረት መስክ የተለዩ የአፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲዎች ርዕያቸውንና ተልዕኮዋቸውን ከማሳካት አንጻር በጋራ መንቀሳቀሳቸው ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያስገኝላቸዋል፡፡

በዛሬው እለት ለምስረታ የሚበቃው የኮንሰርትየም ፎረም በቀጣይ የተለያዩ ተግባራተን በመተግበር ለሌሎችም ማህበራት ሞዴል በሚችል መልኩ ትኩረት ተሰጥቶበት የሚከናወን መሆኑን አንስተዋል፡፡ 

በዚሁ ፎረም ላይ የአፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲዎች የማህበሩ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዱጉማ አዱኛ የቁልፍ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የህግ ት/ቤት ዲን መምህር ዘነበ ሞሼ የማህበሩ የመተዳደርያ ደንብ አቅርበው ውይይት እየተደረገበት ይገኛል፡፡

Share This News

Comment