Logo
News Photo

የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ በራሱ አቅም ያስገነባውን የተማሪዎች የምግብ ቁሳቁሶች ማከማቻ ዘመናዊ መጋዘን አስመረቀ፡፡

የምግብ ቁሳቁሶች ማከማቻ መጋዘኑን መርቀው በይፋ የከፈቱት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም በራስ አቅም የሚሠሩ ስራዎችን ማስፋት ተልዕኳችንን ለማሳካት ትልቅ እገዛ ያደርጉልናል፡፡

ያለንን ውስን ሀብት ተጠቅመን የተማሪዎችን አገልግሎት ለማሳደግ የተሠራው ሥራ የሚበረታታና ወደ ሌሎችም ዘርፎች ሊሠፋ የሚገባው ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በዚሁ የምረቃ ሰነ-ስርዓት ላይ የዩኒቨርሲቲው የአስተዳደር ልማት ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሰለሞን ዘሪሁን የምግብ ቁሳቁስ ማከማቻ መጋዘኖቹን ለመገንባት ከ9.6 ሚሊየን ብር በላይ ተገምቶ የነበረ ቢሆንም በራስ አቅም በተሠራው ስራ ከአንድ ሚሊየን ብር ባነሰ ዋጋ ሥራውን አጠናቆ ለአገልግሎት እንዲበቃ ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል፡፡

እነዚህ በራስ አቅም የሚሠሩ ስራዎች በቀጣይ  በሁሉም ዘርፎች የሚቀጥሉ መሆኑንም ተናግረዋል።  በዚሁም በሥራው ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ ለነበራቸው ሠራተኞች የእውቅና የምስክርወረቀትና የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

በዚሁ የምረቃ ስነ-ስርዓት ላይ በቀጣይ በተመሳሳይ መንገድ ለሚገነባው የተማሪዎች እንጀራ መጋገሪያ  እና ወፍጮ ቤት ግንባታ የማስጀመር ፕሮግራም ተከናውኗል።

Share This News

Comment