ለአካዳሚክ ካውንስል አባላት እና ለተማሪ ተወካዮች 5 million Ethiopian coders ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ
በግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶ/ር መገርሳ ቃሲም በንግግራቸው የ5 million Ethiopian coders የሃገር አቀፍ ተነሳሽነት መሆኑን እና አላማውም የአምስት ሚሊየን ዜጎችን የዲጅታል ሌትሬሲ አቅም በማጎልበት ሃገራችን የያዘችውን የዲጅታል ኢትዮጵያ 2025 እቅድ ለማሳካት እንደሆነ ገልጸው በዚሁ ስልጠና የቀረቡ ኮርሶችን ሁሉም የዩኒቨርስቲያችን ተማሪዎች እና መምህራን እንዲውስዱ ለማድረግ የኮሌጅ ዲኖች፣ የትምህርት ቤቶች ምክትል ዲኖች እና ትምህርት ክፍል ሃላፊዎች ሁኔታዎችን እንዲያመቻቹ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ስልጠናውን የሰጡት የe-learning ዳይሬክተር ዶ/ር ተስፉ ጌትዬ ሲሆኑ በስልጠናውም ለሁሉም አካዳሚክ ካውንስል አባላት እና ለተማሪ ተወካዮች በ5 million Ethiopian coders ፅንሰ ሃሳብ እና ኮርሶች፣ ለኮርሶቹ ለመመዝገብ እና ለመውሰድ የሚያስችሉ ሂደቶች እና ለተማሪዎች እና መምህራን ስልጠናውን እንዲወስዱ ለማድረግ የተዘጋጀ እቅድ እና አተገባበር ላይ ሰፋ ባለመልኩ አቅርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
በእለቱ ሁሉም የስልጠናው ተሳታፊዎች ተመዝግበዋል እንዲሁም ሁሉም ተማሪዎች እና መምህራን ለኮርሶቹ ለመመዝገብ ከጥቅምት 25/2017 እስከ ታህሳስ 19/2017 ዓ.ም እቅድ የተያዘ መሆኑን ተገልጿል፡፡
Share This News