በኢትዮጵያ የUSAID ምክትል ዳይሬክተር የተመራ የልኡካን ቡድን የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ቴክኖሎጂ ማበልጸጊያ ማዕከልን የስራ እንቅስቃሴ ጎበኘ።
በኢትዮጵያ የUSAID ምክትል ዳይሬክተር የተመራ የልኡካን ቡድን የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስና ቴክኖሎጂ ማበልጸጊያ ማዕከልን የስራ እንቅስቃሴ ጎበኘ። በጉብኝቱ ወቅት ለልኡካን ቡድኑ በማዕከሉ እስከዛሬ የተሰሩ ስራዎችን በተመለከተ ሰፋ ያለ ገለጻ የተደረገላቸው ሲሆን በማዕከሉና በOrbit International Hub ድጋፍ የራሳቸውን የቢዝነስ ድርጅት መክፈት የቻሉ ስታርታፖች ስራቸውን እንዲሁም አሁን የደረሱበትን ደረጃ ለልኡካን ቡድኑ አስተዋውቀዋል።
ከጉብኝቱ በኋላ የOrbit International Hub መስራችና የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ፓዚዮን ቸርነት ድርጅታቸው በማዕከሉ ውስጥ ሲሰሩ ለነበሩ ስድስት ጀማሪ ስታርታፖች ያደረገውን የስልጠናና የፋይናንስ ድጋፍ እንዲሁም በቀጣይ በምን መልኩ መደገፍ እንደሚቻል ለልኡካን ቡድኑ ገለጻ አድርገዋል።
በመጨረሻም የልዑካን ቡድኑ አባላት ማዕከሉን እንዲሁም ጀማሪ ስታርታፖቹን መደገፍ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከሚመለከታቸው የዩኒቨርሲቲው አመራሮችና ከጀማሪ ስታርታፖቹ ጋር ተወያይተዋል።
Share This News