Logo
News Photo

በድሬዳዋ አስተዳደር ከሚገኙ ኢንዱስትሪዎች ጋር በቀጣይ በጋራ አብሮ መስራት በሚያስቹሉ ጉዳዮች  ላይ ትኩረቱን ያደረገ የኢንዱስትሪ ፎረም ተካሄደ፡፡


ዛሬ ሐሙስ ጥቅምት 28/2017 ዓ.ም የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ኢንዱስትሪ ትስስርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት ባዘጋጀው ቀጠናዊ የኢንዱስትሪ ትብብር ፎረም ላይ በድሬዳዋ አስተዳደር ከሚገኙ አምራችና አገልግሎት ሰጪ ኢንዱስትሪዎች ጋር ዩኒቨርሲቲው በቀጣይ በጋራ አብሮ መስራት በሚያስቹሉት ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን ያደረገ የኢንዱስትሪ ፎረም ተካሄደ፡፡ 

በፎረሙ ላይ የከፍተኛ ትምህርት፣ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና፣ የምርምር ተቋማት እና የኢንዱስትሪ ትስስር አዋጅ በአቶ ተሾመ ዳንኤል ከት/ት ሚኒስቴር እንዲሁም የኢንዱስትሪዎች የፍላጎት ዳሰሳ ጥናት እና ፕሮግራምን መሰረት ያደረገ የኢንዱስትሪ ማፒንግ ሪፖርት (Program Based Industry Mapping' and Industry demand Assessment Report) በዩኒቨርሲቲው የኢንዱስትሪ ትስስርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በሆኑት ዶ/ር እሸቱ መኮንን አማካኝነት ገለጻ ተደርጓል። 

ከገለጻው በኋላ ዩኒቨርሲቲው እና በአስተዳደሩ የሚገኙ ኢንዱስትሪዎች በቀጣይ እንዴት ተቀራርበው መስራት እንዳለባቸው፣ የኢንዱትሪዎችን ውጤታማነት እና ተወዳዳሪነት በሚጎለብትበት ሂደት የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ምን ሚና መጫወት እንዳለበት እንዲሁም ዩኒቨርሲቲው እንደ አፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲነቱ የሚጠበቅበትን ኃላፊነት በአግባቡ እንዲወጣ ኢንዱስትሪዎች ምን እንደሚጠበቅባቸውና በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ የውይይት መድረክ ተካሂዷል።  

በመጨረሻም በእለቱ ጥሪ የተደረገላቸው የኢንዱስትሪ ተወካዮችና የዩኒቨርሲቲው መምህራን በዩኒቨርሲቲው የሚገኙ ቤተ-ሙከራዎችና ዎርክ-ሾፖች በመጎብኘት ፎረሙ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል፡፡


Share This News

Comment