የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ያዘጋጀውን የተማሪዎች የስብዕና መገንቢያ ማንዋል ዛሬ አስገመገመ፡፡
ቴክኖሎጂ እያደገ በመምጣቱ፣ እንደ ሀገርም ወጣቶችን ለመቅረጽ ብዙ ስራዎች እየተሰራ መሆኑን የገለፁት የዩኒቨርስቲው ፕሬዘዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም እንዳሉት፣ እንደ ዩንቨርስቲ አመራር ተማሪዎቻችን ሀገር ገንቢ፣ ሀላፊነት የሚሰማቸውና ሀገር ተረካቢ እንዲሁም የሀገር ተረካቢ ትዉልድ መሆናቸውን በማመን የበኩላችንን ድርሻ ለመወጣት በርትተን እንሰራለን ብለዋል። ዶ/ር ኡባህ አያይዘውም መሰል ስልጠናዎች ለወደፊትም በስራ አለም ለተማሪዎች ሰፊ እድል እንደሚፈጥርም ተናግረዋል።
በዩኒቨርሲቲው የአስተዳደርና ልማት ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሰለሞን ዘሪሁን በበኩላቸው ለሀገር ጠቃሚና ከስሜት ይልቅ በምክንያት የሚመሩ ተማሪዎች በማፍራት ጉዳት የሚያደርሱ አላስፈላጊ የሆኑ አለመግባባቶችን አስቀድሞ ለማስቀረትም የስብእና መገንቢያ ማንዋሉ ትልቅ ጠቀሜታ ይኖረዋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ስልጠናው ላይ ንግግር ያደረጉት የተማሪዎች አገልግሎት ዲን አቶ ብዙነህ ጅማ፣ ለተማሪዎች አቅም ግንባታ የሚሆኑ ስልጠናዎች ላይ በቱክረት እንደምሰራ ተናግረዋል።
የስልጠናውን ዶክመንት ያቀረቡት የሳይኮሎጂ ዲፓርትመንት መምህር የሆኑት ረ/ፕሮፌሰር ዝናቤ ስዩም፣ ተማሪዎች ከሰው ጋር ያላቸውን ግንኙነት ለማጠናከር፣ ችግሮችን የመፍታት ብቃት እንዲኖራቸውና ራስን የመቻል እንድሁም ለስራ ብቁ የሚያደረግ መሆኑን ገልጸዋል። በተጨማሪም
ከሀረማያ እና ኮተቤ ዩንቨርስቲ ተጋብዘው የመጡ እንግዶች መ/ርት ሜሮን ግዛው እና ዶ/ር አለማው ክፍሌ የዶክመንት ግምገማ አድርገዋል።
ስልጠናውን ያዘጋጁት የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ አስተዳደርና ልማት፣ የተማሪዎች አገልግሎት፣ የሳይኮሎጂ እና ሳይካትሪ ዲፓርትመንት አንድ ላይ በመተባበር መሆኑ ተገልጸዋል።
Share This News