Logo
News Photo

ለድሬዳዋ ዩንቨርስቲ ስራ አስፈፃሚዎች እና ቡድን መሪዎች፣ የዲሲፒሊን እና የስነ-ምግባር ስልጠና ተሰጠ።

"የአንድ ሀገር ስኬት ባንድም በሌላም ከስነምግባር ጋር ይያያዛል። ለአንድ ተቅዋም ስኬትም ሆነ ዉድቀት የሰራተኞቹ ስነምግባር ጉልህ ሚና ይጫወታል" የህግ ት/ቤት ዲን መምህር ዘነበ ሞሼ።

ስነምግባር ሶስት ዘርፎች፣ ማለትም ተግባራዊ ስነምግባር/ applied ethics, ሞያዊ ስነምግባር/professional ethics እና  የስራ ስነምግባር/work ethics መኖሩን የገለፁት የህግ ት/ቤት ዲኑ  አብራርተዋል። 

ተግባራዊ ስነምግባር ስራ ላይም ተጽዕኖ ያለው ሲሆን፣ ሞያዊ  እና የስራ ስነምግባር ደሞ ሀላፊነት እንዲሰማን እንድሁም ለስኬት ያለምነውን ጉጉት ስለሚጨምር፣ ሁሉም ሰራተኞች ሊኖራቻዉ እንደምገባ አንስተዋል።

በተጨማሪም በሁሉም ዘርፎች ላይ ብልሹ አሰራርን ለመቀነስ፣ የደንበኞችን እርካታ ለመጨመር ስነምግባር ያለው ሰራተኛ ያስፈልጋልም ተብሏል።

የስልጠናውን ክፍል ሁለት ያቀረቡት የህግ ት/ቤት መ/ርት ህሊና አሸናፊም የሠራተኞች ግዴታዎች፣አለመግባባቶችና መፍትሄዎች እንድሁም ሌሎች ጉዳዮችን በማንሳት ማብራሪያም ሰተውበታል። 


Share This News

Comment