Logo
News Photo

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የመጀመርያውን የህፃናት ማቆያ ማዕከል አስመርቆ ስራ አስጀመረ፡፡

የድሬደዋ ዩንቨርሲቲ ለመምህራን እና አስተዳደር ሰራተኞች ልጆች ማቆያ የሚሆን ዘመናዊ የህጻናት ማቆያ አስመርቋል። የህጻናት ማቆያውን መርቀው ስራ ያስጀመሩት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም እንደተናገሩት ህጻናት ማቆያው ህጻናት ልጆች ያላቸው የዩንቨርሲቲው መምህራንና እና አስተዳደር ሠራተኞች ተረጋግተው ስራቸውን እንዲሰሩ ትልቅ ሚና ይኖረዋል በለዋል። የህፃናት ማቆያው ለጊዜው 30 ህፃናትን በመቀበል ስራ እንደሚጀምር በመጠቆም በቀጣይ ተጨማሪ ማቆያ ክፍሎችን በመገንባት ተጨማሪ ህጻናትን እንደሚቀበል አስረድተዋል። ስራው ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ከፍተኛ አስተዋጻኦ ያደረጉ ሰራተኞችንም የዩንቨርስቲቲው አፕሬዝደንት ዶ/ር ኡባህ አደም አመስግነዋል። 

 የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ አስገንብቶ በዛሬው እለት ለምረቃ ያበቃው የህፃናት ማቆያ የህፃናት እንክብካቤ የሚደረግብት የመጫወቻ ክፍል፣ የመጀመሪያ ደረጃ የህክምና እርዳታ መስጫ፣ የመጸዳጃ እና የህጻናት መመገቢያ ክፍሎች እንዳሉት ያስረዱት ደግሞ የዩንቨርሲቲው የሴቶች፣ ማህበራዊ ጉዳዮች እና አካቶ ትግበራ ስራ አስጻሚ የሆኑት ወ/ር ዝናሽ ደሳለኝ ናቸው። ወ/ር ዝናሽ በማከልም በተለይ የዩንቨርሲቲው ሴት ሰራተኞች ልጆቻቸውን የሚይዝላቸው ሰው በማጣት ለከፍተኛ እንግልት ተዳርገው የነበሩ መሆኑን ጠቁመው የህጻናት ማቆያው መከፈቱ ለብዙ እናቶች እረፍት መሆኑን ተናግረዋል። 

 የምረቃ ፕሮግራሙ ላይ ጥሪ የተደረገላቸው የዩንቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች፣ የዩንቨርሲቲው መምህራን እና አስተዳደር ሰራተኞች እንዲሁም የፕሮጀክቱ ተጠቃሚ እናቶች እና ልጆቻቸው ተገኝተው የህጻናት ማቆያውን ጎብኝተዋል። 

Share This News

Comment