Logo
News Photo

ለ e-learning ስልጠና ላጠናቀቁ መምህራን በ digital course content development ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ

የስልጠናው መክፈቻ ንግግር ላይ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ የአካዳሚክ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር መገርሳ ቃሲም እንደታናገሩት የኒቨርስቲያችን የመማር ማስተማርን ወደ blended learning እና online learning ለማዘመን የሚያስችሉ የተለያዩ ጉልህ ስራዎች መሰራታቸውን የገለጹ ሲሆን ከነዚህም መካከል 571 መምህራን የe-learning ስልጠና እና 7000 ተማሪዎች ሰባት Student success suit ስልጠናዎች ወስደው በማጠናቀቅ ለe-learning ትግበራ ብቁ የሆኑ ሲሆን በተጨማሪም የመልቲሚዲያ እስቲዲዮ ተሰርቶ ለስራ ዝግጁ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በቀጣይም በሙሉ አቅም ወደ e-learning ትግበራ ለመግባት ትኩረት ከሚሹት ተግባራት መካከል የdigital course content development መሆኑን ገልፀው ሁሉም የe-learning ስልጠና ወስደው ያጠናቀቁ መምህራን በሙሉ እዚህ ተግባር ላይ እንዲሳተፋ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ስልጠናውን የከፈቱት የዩኒቨርስቲያችን ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም ሲሆኑ ጊዜው የቴክኖሎጅ መሆኑ ጠቅሰው እንደ ሀገር የትምህርት ተደራሽነትን እድል ለማስፋት የመማር ማስተማር ሂደትን በe-learning ለመስጠት የተያዘውን አቅጣጭ ዩንቨርስቲያችን በግንባር ቀደምትነት ለመተግበር እካሁን ድረስ የተሰሩ ስራዎች አመርቂ እና የመማር ማስተማሩን በ blended መልኩ ለመስጠት እንደዩኒቨርስቲ ዝግጁ መሆናችንን ገልፀው ለሰልጣኝ መምህራን የሚያስተምሩትን ኮርስ ከ2017 ዓ.ም ሁለተኛ ሴሚስተር ጀምሮ የdigital course content በማዘጋጀት በ blended learning መልኩ መስጠት እንዲጀምሩ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን በትግበራው ጊዜ የሚያስፈጉ ግብአቶችን እና ድጋፎችን ዩኒቨርስቲው እንደሚያደርግ በመናገር ስልጠናውን ከፍተዋል፡፡

ስልጠናውን የሰጡት የe-learning ዳይሬክተር ዶ/ር ተስፉ ጌትዬ ሲሆኑ በስልጠናውም ለሁሉም የe-learning – Master Class: Foundations for Excellence in Teaching Online ስልጠና ያጠናቀቁ መምህራን የዩኒቨርስቲያችንን የe-learning ትግበራ ላይ እስካሁን የተሰሩ ስራዎችን እና የተገኙ ውጤቶችን በአቅም ግንባታ፣ በፖሊሲ እና መመሪያ፣ በLMS SIS ዝግጅት እና አጠቃቀም እና የመልቲሚድያ እስቲዲዮ ግንባታ እና አጠቃቀም ላይ ሰፋ ያለ ገለፃ አድርገዋል፡፡ በመቀጠልም እንደ ሀገር እና ዩኒቨርስቲ የተያዘውን የdigital course content development አቅጠጫ ላይ እና በዩኒቨርስቲያችን በ2017 ዓ.ም ሁለተኛ ወሰነ ትምህርት ኮርሶችን በblended learning መልኩ ለመስጠት የሚስችል የone-one-one እና role model-based digital course content development ፅንሰ ሀሳቦች ላይ ሰፋ ባለመልኩ አቅርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡ 

በእለቱ ሁሉም የስልጠናው ተሳታፊዎች ከስልጠናው መጠናቀቅ በሃላ የተገነባውን መልቲሚዲያ እስቲዲዮ ጎብኝተዋል፡፡

Share This News

Comment