የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መረጃ አስተዳደር (HEMIS) ስልጠና ለድሬደዋ ዩንቨርሲቲ ዝቅተኛ እና መካከለኛ አመራሮች መስጠት ተጀመረ፡
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አጠቃላይ መረጃዎቻቸውን የሚመዘግቡበት የአሰራር ስርዓት (HEMIS) በሁሉም ዩንቨርሲቲዎች ተግባራዊ እየተደረገ ሲሆን የድሬደዋ ዩንቨርሲቲም ይህንኑ የመረጃ አያያዝ ስርዓት ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል። የመረጃ አያያዝ ስራው ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን ለማረም የሚያስችል ስልጠና ደግሞ ለዩንቨርሲቲው አመራሮች መስጠት ተጀምሯል።
ስልጠናውን የከፈቱት የድሬደዋ ዩንቨርሲቲ ፕሬዝዳንድ ዶ/ር ኡባህ አደም እንደተናገሩት ‘’በተቋም ደረጃ ትክክለኛ ዉሳኔ ለመወሰን ትክክለኛ መረጃ ያስፈልጋል’’ ያሉ ሲሆን ‘’ለሚፈለገው አላማ መሰረታዊ መረጃዎች ወቅታቸውን እና ጥራታቸውን ጠብቀው መቅረብ አለባቸው’’ ብለዋል። የተዘጋጀው ስልጠና እንደ ተቋም የተሻለ የመረጃ አያያዝ ስርዓት እንዲኖር ያስችላል ያሉት ዶ/ር ኡባህ የስልጠናዊን ሁለንተናዊ ፋይዳ በመረዳት ተሳታፊዎች በአግባቡ ስልጠናውን እንዲወስዱ አሳስበዋል።
የዩንቨርሲቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር መገርሳ ቃሲም በበኩላቸው ትምህርት ሚኒስቴር በየአመቱ HEMIS ላይ ተመርኩዞ በጀት እንደሚመደብ በመጠቆም ዩንቨርሲቲው በቂ የመንግስት በጀት እንዲመደብለት ወቅታዊ እና የጠራ መረጃ በሚመለከታቸው የዩንቨርሲቲው ሃላፊዎች ሊሞላ ይገባል ብለዋል። ም/ፕሬዝዳንቱ አክለውም በተለይ አዲስ ወደ ኃላፊነት የመጡ እና ነባር የትምህርት ክፍል ኃላፊዎች ጥራት ያለው እና ወቅታዊ መረጃን ሀላፊነት ወስደው መሙላት እንደሚገባቸው አሳስበዋል።
ስልጠናው ለ3 ተከታተይ ቀናት ለትምህርት ክፍል ሀላፊዎች፣ ቡድን መሪዎች፣ አስተባባሪዎች እና መካከለኛ አመራሮች ከትምህርት ሚኒስቴር በመጡ ሁለት ባለሞያዎች እየተሰጠ ይገኛል።
Share This News