Logo
News Photo

በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከሚገኙ አምራችና አገልግሎት ሰጪ ኢንድስቲሪዎች ጋር በዩኒቨርሲቲ ኢንድስትሪ ትስስር ትብብርና ቴክኖሎጂ ሽግግር አስመልክቶ ፎረም ተዘጋጀ፡፡

በዩኒቨርሲቲ ኢንዱስትሪ ትብብርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት አስተባባሪነት በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከሚገኙ አምራች፣ አግልግሎት ሰጪና ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪዎች እና ሌሎች ተቋማት ጋር የውይይት መድረክ ለመፍጠር፣ ትስስርን የሚከፍቱ መንገዶችን ለማፈላለግ፣ የትብብር እንቅፋቶችን ለመለየት፣ የኢንዱስትሪዎችና ተቋማት ፍላጎት እና ክፍተቶች ላይ ተጨማሪ ግንዛቤን ለማግኘት እንዲሁም የወደፊት አቅጣጫዎችን እና መፍትሄዎችን ለመስጠት የምክክር ፎረም በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ውይይት ተካሂዷል።

የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት  የዩኒቨርሲቲው የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሰለሞን ዘሪሁን እንደገለጹት በዩኒቨርሲቲውና በአካባቢው ከሚገኙ ኢንዱስትሪዎች ጋር የተጀመረውን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር እንደሆነ ገልጸው ፎረሙ  ከድሬደዳና አካባቢዋ የመጡ የኮንስትራክሽን አምራችና አገልግሎት ሰጪ ኢንዱስትሪዎች በሚያነሱት ጠቃሚ ሃሳቦች እና እርስ በእርስ በሚፈጠሩት ትስስር ዘርፉ  ውጤታማ በማድረግ ትልቅ እገዛ እንደሚኖረው ተናግረዋል፡፡

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም በበኩላቸው ፎረሙን በይፋ መከፈቱን በማብሰር ዩኒቨርሲቲውና በኢንዱስትሪው መካከል ትስስር መፈጠሩ ዘርፈ ብዙ ጥቅም እንዳለው ገልጸው  በተለይም ለገበያው ተፈላጊውንና ብቁ የሰው ኃይልን በማፍራት በጥናትና ምርምር ለሀገር ለውጥ ለማምጣት የሚችሉ ተግባራትን ለማከናወን ትልቅ እድል እንደሚፈጥርም አስታውቀዋል፡፡ 

ዶ/ር ኡባህ አክለው ሃገራችን ከድህነት እና ከኋላ ቀርነት ተላቃ የተሻለ እድገትና ለውጥ ማስመዝገብ እንድትችል በኢንዱስትሪው ዘርፍ በጥናትና ምርምር አዳዲስ የፈጠራዎችን እና የቴክኖሎጂ ግኝቶችን  በማፍለቅ ህዝባችንን ሊጠቅሙ የሚችሉ ተግባራትን በማከናወን እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡ 

በዚሁ ፎረም ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የድሬደዋ አስተዳደር የንግድ፣ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ምክትል የቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ አብዲ ሙክታር እንዳሉት በኢንዱስትሪው ማደግና ወደ ላቀ ደረጃ ላይ መድረስ ከዩኒቨርሲቲው ጋር ቁርኝት መፍጠሩ ትልቅ ፋይዳ እንደሚኖረው ገልፀው አስተዳደሩም ለዚህ ስኬት መምጣት የጀመረውን ድጋፍ በሁሉም መልክ አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡

በመድረኩ ላይ ሁለት ሰነዶች ለውይይት ቀርበው ጥልቅ እና አስተማሪ ውይይት የተካሄደ ሲሆን ከሰማንያ በላይ የሚሆኑ ከአምራች፣ አግልግሎት ሰጪ እና ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪዎች የተወከሉ ተሳታፊዎች እንደተገኙ ታውቋል፡፡

በመጨረሻም የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ እና የድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፖርክ የጋራ የመግባቢያ ሰነድ የተፈራረሙ ሲሆን የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም እንዲሁም በድሬዳዋ ኢንደስትሪ ፓርክ የተቋሙ ስራ አስኪያጅ አቶ ካሚል ኢብራሂም የመግባቢያ ሰነዱ ላይ ፊርማቸውን አኑረዋል፡፡ 


Share This News

Comment