Logo
News Photo

በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የአሊ ቢራ የሙዚቃ ት/ርት ቤትን ለማቋቋም የሚያስችል የዝግጅት ስራ ተካሄደ፡፡ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ያሬድ ሙዚቃ ት/ርት ቤት የመጡ ምሁራን ልምድ እና ተሞክሯቸውን ለድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች አጋርተዋል፡፡

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በታላቁ አርቲስት የክብር ዶ/ር አሊ ቢራ ስም የተሰየመ የሙዚቃ ት/ርት ቤት ለማቋቋም ሰፊ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ የዚሁ ስራ አካል የሆነ እና ምርጥ ተሞክሮዎችን ከአቻ ተቋማት የመቀመር ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ያሬድ ሙዚቃ ት/ርት ቤት የመጡ ምሁራን እና የት/ርት ቤቱ አመራሮች የሙዚቃ ት/ርት ቤቱን ለማቋቋም በሚያስፈልጉ የቁሳቁስ እና የሰው ሃይል ግብዓቶች ዙሪያ ልምዳቸውን አጋርተዋል፡፡ 

በዶ/ር መላኩ ይገዙ የሚመራው የያሬድ ሙዚቃ ት/ርት ቤት ለዑካን ቡድን በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ለሚያቋቁመው የሙዚቃ ትምህርት ቤት አስፈላጊውን ሁሉ እገዛ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል፡፡ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ም/ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶ/ር መገርሳ ቃሲም ድሬዳዋ የበርካታ ሙዚቀኞች እና የጥበብ ባለሙያዎች ከተማ መሆኗን አስታውሰው አዲስ የሚከፈተው የሙዚቃ ት/ርት ክፍል ይህንኑ አካባቢያዊ ፀጋ መሰረት አድርጎ የሚቋቋም መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ 

ከያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት የመጡ ባለሙያዎች የዩንቨርስቲውን የማህበረሰብ ተኮር ኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያንም ጎብኝተዋል፡፡በጉብኝታቸውም ወቅት ኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያው  የድሬዳዋ ዩንቨርሲቲ ለሚከፍተው የአሊ ቢራ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ጥሩ ግብዓት እንደሚሆን ጠቁመዋል፡፡

Share This News

Comment