የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራር የፋሲካን በዓል ከተማሪዎች፣ ከፌደራል ፓሊስ አባላት እና የአካባቢው ማህበረሰብ ተወካዮች ጋር በመሆን በደማቅ ሁኔታ አክብሯል። የፋሲካን በዓል በተማሪዎች መመገቢያ አዳራሽ ተገኝተው ያከበሩት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም ተማሪዎቻችን እንኳን ለፋሲካ በዓል በሰላም አደረሳችሁ የሚል መልዕክታቸውን ያስተላለፉ ሲሆን በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር እና የደስታ እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን በራሳቸው እና በመላው የዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንት አባላት ስም አስተላልፈዋል።
የፌደራል ፓሊስ አባላት እና የአካባቢው ማህበረሰብም የፋሲካን በዓል በድምቀት ያከበሩ ሲሆን የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራር በዚሁ የበዓል መርሃ ግብር ላይ ተገኝተው በዓሉን በጋራ አክብረዋል። የፌደራል ፓሊስ አባላት ባዘጋጁት የምሳ ፕሮግራም ላይ የተገኙት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም ንግግር ያደረጉ ሲሆን ‘’የፌደራል ፓሊስ አባላት እና የአካባቢው ማህበረሰብ ዩኒቨርሲቲው ሰላማዊ እና የተደረጋጋ የመማር ማስተማር ስራን እንዲሰራ ላበረከቱት የላቀ አስተዋጻኦ አመስግነው ለመላው የፌደራል ፓሊስ አባላት መልካም የፋሲካ በዓል እንዲሆን ተመኝተዋል።
Share This News