Logo
News Photo

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያ እና ሪፈራል ሆስፒታል ከ ሂዩማን ብሪጅ (Human Bridge) ያገኛቸውን የህክምና መገልገያ መሳሪያዎችን ተረከበ።

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያ እና ሪፈራል ሆስፒታል ዋጋቸው 60 ሚሊየን ብር በላይ የሆነ የህክምና ቁሳቁሶችን በእርዳታ ማግኘቱ የሚታወስ ሲሆን ቁሳቁሶቹን የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች እና ሂዩማን ብሪጅ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት በይፋ ተረክቧል።

የህክምና ቁሳቁሲቹን የተረከቡት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት / ኡባህ አደም ሂዩማን ብሪጅ ሆስፒታሉ በፍጥነት ተደራጅቶ ስራ እንዲጀመር ከፍተኛ ዋጋ ያላቸው እና በቀላሉ ገበያ ውስጥ የማይገኙ የህክምና መሳሪያዎችን በማበርከት ላደረገው ከፍተኛ አስተዋፅኦ በማመስገን ሆስፒታሉን በሙሉ አቅሙ ስራ ለማስጀመር በሚደረገው ጥረት ውስጥ የድርጅቱ ሚና የጎላ በመሆኑ ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀትል ጥሪ አስተላልፈዋል።

/ አዳሙ አንለይ የሁማን ብሪጅ ካንትሪ ድይሬክተር ሲሆኑ የህክምና ቁሳቁሶቹን ድሬዳዋ በመገኘት አስረክበዋል። / አዳሙ በርክክቡ ወቅት እንደተናገሩት ‘’ ሂዩማን ብሪጅ በስዊድን ሀገር የሚገኝ ግብረሰ ሰናይ ድርጅት መሆኑ ጠቁመው ድርጅቱ 50 የተለያዩ ሀገራት ቅርንጫፎችን ከፍቶ በተለይ ከህክምና አገልግሎት ጋር የሚስተዋለውን የህክምና መገልገያ ቁሳቁስ ችግር ለመፍታት ስራዎችን እየሰራ ያለ ድርጅት መሆኑን ጠቁመዋል።

/ አዳሙ በማከልም ሂዩማን ብሪጅ የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያ ሪፈራል ሆስፒታልን ለመደገፍ አሁንም ዝግጁ መሆኑን የተናገሩ ሲሆን በቀጣይ ሆስፒታሉ የሚጎሉትን ቁሳቁሶች በማሟላት የተሟላ የህክምና አገልግሎት ለአካባቢው ማህበረሰብ እንዲሰጥ የበኩሉን ጥረት እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያ ሪፈራል ሆስፒታል የህክምና መገልገያ ቁሳቆሶቹ እንዲገኙ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱት ሂዩማን ብሪጅ ግብረ ሰናይ ድርጅት እና ቁሳቁሶቹ ያለምንም ቀረጥ እና እንግልት ሀገር ውስጥ ገብተው ጥቅም ላይ እንዲውሉ አበርክቶ ለነበረው የፌደራል ጉምሩክ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ /ቤት ልዩ የምስጋና የምስክር ወረቀት ተበርክቷል።

 

Share This News

Comment