Logo
News Photo

"ሁሉን አካታች ብሔራዊ ውይይት ለሀገራዊ መግባባትና ለዘላቂ ልማት" በሚል ርዕስ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ተካሄዷል፡፡

የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ያዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ላይ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር የሰላም ግንባታ ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ ክቡር አቶ ታዬ ደንደአ፣ የድሬደዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሀር፣ የድሬደዋ አስተዳደር የብልጽግና ጽ/ቤት ኃላፊ ክቡር አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ፣ የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም እንዲሁም የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች፣ የሃገር ሽማግሌዎች፣ የተለያዩ አደረጃጀት ማህበራት፣ የፓለቲካ ፓርቲ አባላት እንዲሁም በመድረኩ ላይ ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡ 

የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ ለግማሽ ቀን የቆየ ሲሆን በመድረኩላይ የተለያዩ ጥናታዊ ጽሁፎች በምሁራን ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

Share This News

Comment