Logo
News Photo

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ሰራተኞች የእግር ኳስ ጤና ቡድን ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሰራተኞች እግር ኳስ ጤና ቡድን ጋር የወዳጅነት ግጥሚያ አደረገ፡፡

የጤና ቡድኑ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ጤና ቡድን በቀረበለት ጥሪ ሀዋሳ በመገኘት ባደረገው ጨዋታ 4 ለ 1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል፡፡ 

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የእግር ኳስ ጤና ቡድን ዩኒቨርሲቲው ከተመሰረተበት ግዜ (1999 ዓ.ም) ጀምሮ ተቋሙን በመወከል ከተለያዩ ተቋማት ጤና ቡድን ጋር ውድድሮችን  እያከናወነ ያለ ሲሆን በድሬዳዋ ከተማ በየዓመቱ በአስተዳደሩ ስፖርት ኮሚሽን አዘጋጅነት በተቋማት መካከል በሚደረገው ውድድር ላይ በቋሚነት ሲሳተፍ ቆይቷል፡፡


Share This News

Comment