የተማሪዎችን የሥራ ፈጠራ አቅም ለማጎልበት የተዘጋጀ ስልጠና ተካሄደ።
ተመራቂ ተማሪዎች (GC) እንዲሁም ከየባቹ ለተመረጡ ተማሪዎች የሥራ ፈጠራ ክህሎት ልማት (Entrepreneurship Skill Development) ስልጠና ተሰጥቷል። ስልጠናው የተማሪዎችን የፈጠራ አቅም ወደ ተጨባጭ ኢኮኖሚያዊ ውጤት ለመቀየር ያተኮረ ሲሆን፣ ተማሪዎች ከሥራ ፈላጊ ወደ ሥራ ፈጣሪነት እንዲሸጋገሩ እንደሚያግዝ ተጠቁሟል።
ስልጠናው በተለይ የተማሪዎችን የሥራ ፈጠራ አስተሳሰብ፣ የንግድ እድሎች መለየት እና የሀሳብ ልማት፣ የንግድ ሞዴል እና የንግድ እቅድ አዘጋጅት፣ የፋይናንስ አስተዳደር እና የሀብት ምንጭ መፈለግ፣ ፈጠራ፣ ዲጂታል መሣሪያዎች እና የንግድ ማስተዋወቅ፣ የንግድ ህጋዊ እና ስነ-ምግባራዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ሰፊ ግ ንዛቤ እና ክህሎትን የፈጠረ ሆኗል፡፡
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የሥራ ዕድል ፈጠራና ልማት ማዕከል (CEED) ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ቃልኪዳን መዝገቡ ባስተላለፉት መልዕክት ''ስልጠናው የተማሪዎችን የፈጠራ አቅም ወደ ተጨባጭ ኢኮኖሚያዊ ውጤት ለመቀየር ያተኮረ ነው'' ያሉ ሲሆን ተማሪዎች ስልጠናውን በንቃትና በትኩረት እንዲከታተሉና ከሥራ ፈላጊ ወደ ሥራ ፈጣሪነት እንዲሸጋገሩ መል ዕክት አስተላልፈዋል።
የስልጠናውን መጠናቀቅ አስመልክቶ የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ምክትል ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ ዶ/ር በረከት ተስፋዬ ለአሰልጣኞች እና ተሳታፊ ተማሪዎች የምስክር ወረቀት ተሰጥቷል።
ዶ/ር በረከት በዚሁ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት ፕሮግራሙ በዩኒቨርሲቲው ውስጥ የሥራ ፈጠራ ባህልን ለማጠናከር እንዲሁም ተማሪዎች ከትምህርት በኋላ ወደ ተግባራዊ ሥራ እንዲገቡ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ተገልጸው ስልጠናውን ያዘጋጀውን የሥራ ዕድል ፈጠራና ልማት ማዕከል (CEED) ዳይሬክቶሬት አመስግነዋል፡፡
Share This News