Logo
News Photo

ቅይጥ የማስተማሪያ ዘዴን በመጠቀም ላስተማሩ መምህራን እውቅና ተሰጠ፡-

የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ የመማር ማስተማርን በblended እና online መልኩ በመስጠት የትምህርትን ጥራትና ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ሰፊ ስራ እየሰራ ሲሆን በ2018 የመጀመሪያ ወሰነ ትምህርት በ23 ፕሮግራሞች ስር ያሉ 25 ኮርሶችን በblended መልኩ ከ2000 በላይ ለሆኑ ተማሪዎች ትምህርት መስጠት ችሏል፡፡ 

ዩኒቨርሲቲው ትምህርቶቻቸውን በቅይጥ የማስተማሪያ ዘዴ (ከፊል ትምህርት በመማሪያ ክፍል ውስጠ ከፊሉን ደግሞ በበይነ መረብ በመታገዝ የሚሰጥ ትምህርት) በመጠቀም ላስተማሩ መምህራን እውቅና ሰጥቷል፡፡ 

በእውቅና አሰጣጥ መርሃ ግብሩ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ግርማ ቤካ ‘’ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በe-learning አተገባበር እና ዘመናዊ የመማር ማስተማር ዘደዎችን በመጠቀም ረገድ ባሳየው ግንባር ቀደም ስራ በሀገር አቀፍ ደረጃ እወቅና እያገኘ ያለ ተቋም ነው’’ ብለዋል፡፡ 

የኤሌክትሮኒክ ትምህርት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ተስፉ ጌትዬ በበኩላቸው ዩኒቨርስቲያችን እስካሁን ድረስ የሰራቸውን ስራዎች “E-learning Practices and Implementation at DDU” በሚል ገለፃ ያካሄዱ ሲሆን በዚሁም 990 መምህራን የmaster class ስልጠና ማጠናቀቃቸውን፣ 13,029 ተማሪዎች የSSS ስልጠና መውሰዳቸውን እና በ32 ፕሮግራሞች ስር ያሉ 43 ኮርሶችን በblended መልኩ ትምህርት መሰጠቱን አመልክተዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በ2018 ዓ/ም የትምህርት ዘመን በ ትምህርት ዘመኑ የመጀምሪያ ወሰነ ትምህርት በ blended መልኩ ትምህርት ለሰጡ 29 መምህራን የእውቅና ሰርትፍኬት ከምስጋና ጋር ሰጥቷል፡፡

Share This News

Comment