የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በእንግሊዘኛ ቋንቋ ማሻሻያ ፕሮግራም (ELIP) ያሰለጠናቸውን 39 መምህራን አስመረቀ
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ለሦስት ወራት በእንግሊዘኛ ቋንቋ ክህሎት ማሻሻያ መርሃ ግብር ያሰለጠናቸውን 39 መምህራን አስመርቌል። ዩኒቨርሲቲው የመምህራኑን አቅም የሚገነቡ እንዲሁም የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የሚያግዙ በርካታ የአቅም ማሻሻያ ስልጠናዎችን በመስጠት ላይ የሚገኝ ሲሆን የዩኒቨርሲቲውን መምህራን የእንግሊዘኛ ቋንቋ ክህሎት ለማሻሻል ያለመ የ3 ወር ስልጠና በመስጠት አስመርቋል፡፡
በምርቃቱ ላይ የተገኙት የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ም/ ፕሬዚዳንት ዶ/ር መገርሳ ቃሲም ስለ ፕሮግራሙ ጠቀሜታ ሲያብራሩ መንግስት እንደ ሀገር የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ጠቁመው የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲም ይህንኑ ሀገራዊ ተልዕኮ ለማሳካት በ2018 ዓ.ም አሳካቸዋለው ብሎ ካቀዳቸው KPI ውስጥ በማካተት እና ዝርዝር ቁልፍ ተግባራትን በመለየት ወደ ስራ ገብቷል ብለዋል፡፡ ዶ/ር መገርሳ አክለውም መሰል የቋንቋ ማሻሻያ ስልጠናዎች ዩኒቨርሲቲው ጥራት ያለው ትምህርትን ለመስጠት ያግዛል ያሉ ሲሆን ለዚህ ፕሮግራም መሳካት በአሰልጣኝነትና በአዘጋጅነት ድርሻቸውን ለተወጡ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።
የዩኒቨርሲቲው የእንግሊዘኛ ቋንቋ ማሻሻያ ፕሮግራም (ELIP) አስተባባሪ መ/ር ነቢል መሀመድ በበኩላቸው የቋንቋ ማሻሻያ ማዕከሉ አዲስ ሰልጣኝ መምህራንን በመቀበል ስልጠናውን በተጠናከረ መልኩ መስጠቱን እንደሚቀጥል በመጥቀስ በፕሮግራሙ ላይ የተገኙ የሁለተኛ ዙር ሰልጣኞችን እንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
Share This News