ለድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በሙሉ
በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በ2012 ዓ.ም የወጣና በስራ ላይ ያለ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የዲሲፕሊን መመሪያ መኖሩ ይታወቃል፡፡ ስለሆነም በመመሪያው የተከለከሉ ነገሮችን እንደሚከተለው በመዘርዘር እነዚህን ክልከላዎች ተላልፎ የተገኘ ተማሪ በመመሪያው ላይ ለጥፋቱ የተቀመጠው እርምጃ እንደሚወሰድበት እናሳውቃለን፡፡
አንቀጽ 7፡ የተከለከሉ ተግባራት
1. በማንኛውም ሁኔታ በተቃራኒ ጾታ ላይ በደል ወይም ጾታዊ ትንኮሳ መፈጸም
2. በግቢ ውስጥ ሆኖ ማንኛውንም አይነት ሀይማኖታዊይም ይሁን ፖሊቲካዊ እንቅስሴ ማድረግ
3. ሀይማኖትን፣ ብሄርን፣ ባህልንና ቋንቋን የሚያንቋሽሽ ማንኛውንም ንግግር ማድረግ፣ መፃፍ ወይም ድርጊት መፈፀም
4. ፖለቲካዊና ሀይማኖታዊ መልዕክት ያላቸውን አልባሳት፣ ቅርፆች፣ ጌጣጌጦች፣ የተለያዩ ቦርሳዎችና እቃ መያዣዎች መጠቀም
5. ወደ ግቢ ውስጥ ማንኛውም አይነት አደንዛዥ እፅ ማዛወር፣ ይዞ ወይም ተጠቅሞ መገኘት፣ አልኮል ጠጥቶ ወይም ሰክሮ መግባት
6. የዩኒቨርሲቲውን ሰራተኞች በምንም ሁኔታ መሳደብ፣ መዝለፍ፣ ማንጓጠጥ፣ ማስፈራራትና መዛት ያልተገባና ፀያፍ ንግግር መናገር
7. የሌሎች ተማሪዎችን ማህበራዊ ኑሮ የሚያውኩ ድርጊቶችንና ንግግሮችን መፈፀም፣ መረበሽ፣ ቁማር መጫወት
8. ማንኛውም የስርቆት ተግባር መፈፀም
9. አደጋ የሚያደርስ ማንኛውንም ነገር ለምሳሌ ስለት ያለው መሳሪያ፣ መርዝ ይዞ ወደ ግቢ ወይም አገልግሎት መስጫ ቦታዎች መግባት
10. ከመፀዳጃ ቤቶች ውጭ መፀዳዳት
11. በማንኛውም አካል የሚለጠፍ ህጋዊ ማስታወቂያን መገንጠል፣ መቅደድና መሰረዝ
12. በአገልግሎት ዙሪያ ቅሬታ ሲኖር በሰላማዊና በህጋዊ መንገድ መጠየቅ እንጅ አመፅ ማንሳት፣ ማነሳሳት፣ መተባበር
13. በማንኛውም የዩኒቨርሲቲው ንብረት ላይ ጉዳት ማድረስ
14. ፀጉርን በተመለከተ፡
14.1. ለወንዶች፡ ከ1.5ሴንቲ ሜትር ያልበለጠ ሆኖ ምንም አይነት ቅርፅ የሌለው
15.2. ለሴቶች፡ በአግባቡ የተሰራና ያልተንጨባረረ
15. አለባበስን በተመለከተ፡
ለወንዶች፡ የተቦጫጨቀ፡ የተቀደደ፣ ገላን የሚያሳይ ልብስ መልበስ፣ ሱሪን ዝቅ በማድረግ የውስጥን ቁምጣ ማሳየት፣ ሌላን ሰው ሊረብሽ የሚችል ከፍተኛ ሽታ ያለው ሽቶ፣ ዲኦዶራንት እና ሌሎችም መጠቀም
ለሴቶች፡ የተቦጫጨቀ፣ የተቀደደ፣ ገላን የሚያሳይ ልብስ መልበስ፣ ከጉልበት በላይ ያጠረ ቀሚስ መልበስ፣ ሌላን ሰው ሊረብሽ የሚችል ከፍተኛ ሽታ ያለው ሽቶ፣ ዲኦዶራንት እና ሌሎችም ኮስሞቲክስ መጠቀም፣ ከፍ ያለ ድምፅ የሚያወጡ ጫማዎችን መጫማት
16. ባልተፈቀደ በር ወይም አጥር ዘሎ መግባትና መውጣት
17. የጋራ/የወል መገልገያዎችን የግል ማድረግ
አንቀጽ 8፡ በተማሪዎች መኝታ ቤት የተለከለከሉ ተግባራት
1. የዩኒቨርሲቲው ያልሆነ ወይም የተባረረ ተማሪ መኝታ ቤት ማሳደር፣ ማኖር
2. ተደራራቢ አልጋዎችን መገንጠል፣ ፍራሽ መሬት ላይ አውርዶ መተኛት
3. በተቃራኒ ጾታ መኝታ ክፍል መግባት፣ ማስገባት
4. በህመም ምክንያት ካልተፈቀደ በስተቀር ምግቦችን ወደ መኝታ ክፍል ይዞ መግባት
5. የመኝታ ቤት ቁልፍ በሚመለከተው አካል ሳይፈቀድ ማስቀረጽ
6. በአንድ አልጋ ላይ ከአንድ በላይ ሆኖ መቀመጥ፣ መተኛት
7. በመስኮት መውጣት ወይም መግባት
8. በማንኛውም ጊዜ በመኝታ ክፍል ውስትና አካባቢ ጫጫታና ረብሻ መፍጠር፣ የሚረብሽ ድምጽ/ሙዚቃ፣ የሞባይል መጥሪያ ማሰማት
9. የሽንት ቤትና ሻወር ቤቶች፣ የልብስና እጅ መታጠቢያ ገንዳዎችን፣ ማስረጊያ ቀዳዳዎችን አላስፈላጊ የሆኑ ፕላስቲክ፣ ድንጋይ፣ ጸጉር፣ ጨርቅና ሞዴስ፣ ወዘተ ነገሮችን በመክተት እንድዘጉ ማድረግ፣ መብሳትና መቅደድ
10. በመኝታ ክፍል ውስጥ አልጋን መጋረድ/ቴንሽን ቦክስ መስራት
11. ባልታወቀ ሁኔታና ሳይፈቀድ በዶርም ውስጥና አካባቢ ስብሰባ ማድረግና ሰፊ ቁጥር ይዞ በቡድን መንቀሳቀስ
12. በዶርም ውስጥና አካባቢ በቡድን ሆኖ መጸለይ ወይም መስገድ
13. በዶርም ውስጥ ምግብ ማብሰል፣ ሻይና ቡና ማፍላት
14. ከተመደቡበት ዶርም ውጭ ያለፈቃድ መቀየር
15. በሽንት ቤትና በሻወር ቤት ውስጥ ያልተገቡ ጽሁፎችን መፃፍ/መለጠፍ
16. ባልተመደቡበት የመኝታ ክፍል ውስት ተዳብሎ መተኛት ወይም አዳብሎ ማስተኛት
17. በግድግዳዎች፣ መስኮቶች፣ መዝጊያዎች እና ቁምሳጥኖች ላይ ማንኛውንም ጽሁፍ መፃፍ፣ ስዕል መሳል/መለጠፍ፣ ሚስማር መቸከል/መምታት
18. በመኝታ ቤት ውስጥና አካባቢ ጫት፣ ሲጋራ፣ አልኮል መጠጦችን እና ሌሎች አደንዛዥ እፆችን ይዞ መግባት ወይም ሲጠቀሙ መገኘት
19. የተቆለፉ መኝታ ክፍሎችን ወይም የሌሎች ተማሪዎችን በር ያለፈቃድ መክፈት/መስበር
20. በዶርም ውስጥ ልብስ ማጠብ
አንቀጽ፡ 9፡ በተማሪዎች ምግብ ቤት የተከለከሉ ተግባራት
1. የራስ ባልሆነ መመገቢያ ካርድ መመገብና የራስን የመመገቢያ ካርድ ለሌላ አካል አሳልፎ መስጠት
2. ወደ ምግብ ቤት የአንገት ፎጣ፣ ኮፍያ፣ ሲሊፐር ጫማ፣ የሌሊት ልብስ ፒጃማ እና ሎሎች ተገቢ ያልሆኑ ልብሶችን እና አለባበሶችን ለብሶ መምጣት
3. በምግብ አዳራሽ ውስጥና አካባቢ ከሰራተኞች ወይም ከተማሪዎች ጋር ግጭት መፍጠር፣ ሰልፍ መጣስ
4. በምግብ ዙሪያ ጥያቄ/ቅሬታ ሲኖር በተወካይ አለያም በራስ ስርዓትን ጠብቆ ለሚመለከተው አካል ማቅረብ እንጅ ያልተገባ ባህሪ ማሳየት፣ ሁከት መፍጥር ወይም እንድነሳ ማድረግ
5. በምግብ አዳራሽ ውስጥ እጅን መታጠብ
6. በህመም ምክንያት መንቀሳቀስ ከማይችሉ ተማሪዎች በስተቀር ከዳቦ ውጭ ምግብ ከተማሪዎች ምግብ ቤት ማውጣት
7. ከቀረበው የምግብ አይነት ውጭ የሀኪም ትዕዛዝ ካላቀረቡ በስተቀር መጠየቅ፣ መጨቃጨቅ፣ መጣላት
Share This Event