Logo
News Photo

የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ ተኮር የሬድዮ ጣቢያ ተመረቀ፡፡

የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ከፋና ብርድካስት ኮርፖሬት ጋር በገባው ውል መሠረት አስገንብቶ ለአገልግልት ያበቃው የማህበረሰብ ተኮር የሬድዮ ጣቢያ ዛሬ በይፋ ተመርቆ መደበኛ የሙከራ ስርጭቱን ጀምሯል፡፡

በሬድዮ ጣቢውን የምረቃ ስነ-ስርዓት ላይ የድሬደዋ አስተዳደር ከንቲባ የተከበሩ አቶ ከድር ጁሀር የሬድዮ ጣቢያው መከፈት በድሬደዋ የተጀመረውን ሁለንተናዊ እድገት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የበኩሉን ድርሻ ይወጣል ብለዋል፡፡

በተለይም አሁን ያለንበት ዘመን  የመረጃ ዘመን እንደመሆኑ የተሟላና ትክክለኛ መረጃን ለማህበረሰቡ በማድረስ ምክንያታዊ አመለካለት ያለው ማህበረሰብን በመፍጠር አድግት እንዲመዘገብ ትልቅ አቅም ይፈጥራል ብለዋል፡፡

"የሬድዮ ጣቢያው መቋቋም  ማህበረሰቡን ከቀድሞ በበለጠ መቅረብ የምንችልበት እድል የሚፈጥርልን ነው " ያሉት የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም ጣቢያው የሙከራ ስርጭቱን አጠናቆ መደበኛ የአየር ላይ ስርጭት ሲጀምር በአራት ቋንቋዎች (በአማርኛ ፣ በኦሮምኛ ፣በሶማልኛ እና በእንግሊዘኛ ) የ18 ሰዓት የአየር ላይ ስርጭት  እንደሚኖረው ተናግረዋል፡፡

የፋና ብሮድካስት ኮርፖሬት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አድማሱ ዳምጠው በበኩለካቸው ፋና ብሮድካስት ኮርፖሬት በሁሉም መልኩ ዩኒቨርሲቲው በቀጣይ ለሚያከናውናቸው እንቅስቃሴዎች የጀመረውን ተቀራርቦ የመስራትና እገዛ የማድረግ ተግባሩን አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡

በመጨረሻም የሬድዮ ጣቢየውን ከመነሻው ጀምሮ   እስካሁን ድርስ የነበረውን ሂደት እንዲሁም በቀጣይ የሚኖረውን መድረሻ የሚያስቃኝ ጥናታዊ ጽሁፍ በዩኒቨርሲቲው ጆርናሊዝም እና ኮሚኒኬሽን ትምህርት ክፍል ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን ለሬድዮ ጣብያው መቋቋም የተለያዩ እስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት የእውቅና የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋለ፡፡

Share This News

Comment