Logo
News Photo

በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ የመሬትና ቋሚ ንብረት ግመታ ትምህርት ክፍልን ከባለድርሻ አካላት ጋር ማስተሳሰር ላይ ታሳቢ ያደረገ የጋራ የውይይት መድረክ ተካሄደ፡፡

በጋራ የውይየት መድረኩ ላይ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት በዩኒቨርቲዉ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሰለሞን ዘሪሁን እንዳሉት መሬትና ቋሚ ንብረቶች በሀገር ምጣኔሀብታዊ እድገት ላይ የሚጫወቱት ሚና እጅግ ከፍተኛ በመሆኑ ይህን ዘርፍ በትኩረትና በዘመነ መልኩ ልንመራው ይገባል፡፡

በዚህ ረገድም ዩኒቨርሲቲው ከባለድርሻ አካለት ጋር ተቀራርቦ የሚሰራቸው ስራዎች ለሁለቱም ወገን ከፍተኛ ጥቅም የሚያስገኝ በመሆኑ ይህ ጅምር ቅንጅታዊ አካሄድ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባዋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

 በመድረኩ ላይ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደርና የተማሪዎች ጉዳይ ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር አብርሃም እውነቱ በበኩላቸው መሬት ውስን ሀብት በመሆኑ ይህን ውስን ሀብት በአግባቡ በመጠቀም የጀመርነውን ልማት ቀጣይንት በማረጋገጥ እድገትን ማስመዝገብ ከሁላችንም ይጠበቃል ብለዋል፡፡

በተለይም መድረኩ በትምህርት ክፍሉ ትምህርታቸውን ላጠናቀቁም ሆነ ትምህርታቸውን  በመከታተል ላይ ለሚገኙ ተማሪዎች በርካታ ጥቅም የሚያስገኝ በመሆኑ ዩኒቨርሲቲው በድሬደዋ አስተዳደር እና በአጎራባች ክልሎች ከሚገኙ ባለድርሻ አካለት ጋር የሚፈጥረው ትስስር ሳይቋረጥ መቀጠል ይኖርበታል ብለዋል፡፡

በዩኒቨርሲቲው የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ የመሬትና ቋሚ ንብረት ግመታ ትምህርት ክፍል ያዘጋጀው የጋራ የውይይት መድረክ ትምህርት ክፍሉ ከተለያዩ ባለድርሻ አካለት ጋር በማገናኘት ትስስር ማጠናከር ላይ ትኩረት ያደረገ መሆን የገለፁት በዩኒቨርቲው የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ዲን የሆኑት ረዳት ፕሮፌሰር ነፃነት ሽፈራው ናቸው፡፡ 

የአሁኑ መድረክ ዘንድሮ ለሁለተኛ ጊዜ የተዘጋጀ መሆኑን የጠቀሱት ረዳት ፕሮፌሰር ነፃነት በቀጣይም ትምህርት ክፍሉን ከባለድርሻ አካላት ጋር የሚያገኛኝ ተመሳሳይ መድረክ በማዘጋጀት በዘርፉ ትልቅ አቅም የሚፈጠርበት ስራ ይሰራል ብለዋል፡፡

ለአንድ ቀን የቆየውና በዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ የመሬትና ቋሚ ንብረት ግመታ ትምህርት ክፍልን ከቀጣሪ ድርጅቶች፣ ከባለድርሻ አካላት እና  ከኢንዱስትሪዎች ጋር ለማስተሳሰር በታሰበ የተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ከፌደራል ትምህርት ሚኒስትር፣ ከከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር፣ ከፐብሊክ ሰርቪስ ኮሚሽን፣ ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር እንዲሁም ከተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ  ተቋማት የተወከሉ ተሳታፊዎች በመድረኩ ላይ ተካፋይ ሆነውበታል፡፡

Share This News

Comment