Logo
News Photo

የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ለ2014 ዓ.ም አዲስ ገቢ ሴት ተማሪዎች የእንኳን ደህና መጣቹህ አቀባባል አደረገ፡፡

በእንኳን ደህና መጣቹህ አቀባበል ስነ-ስርዓቱ ላይ ተገኝተው ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች መልእክት ያስተላለፋት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም እንደገለጹት ሴት ተማሪዎች ሊገጥሟቸው የሚችሉ ፈተናዎችን በፅናት ተቋቁመው በትምህርታቸው ውጤታማ መሆን ይገባቸዋል ብለዋል፡፡

በተለይም ከመጡበት ዓላማ ሊያሰናክሏቸው ከሚችሉ እንቅፋቶች ራሳቸውን በማቀብ እና በመጠበቅ ሙሉ ትኩረታቸውን ትምህርታቸው ላይ ብቻ በማድረግ ከራሳቸው አልፈው ለሀገር የሚጠቅሙ ዜጋ መሆን ገልጸው ለዚህ ደግሞ ዩኒቨርሲቲው አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍና እገዛ ያደርጋል ብለዋል፡፡

በዩኒቨርሲቲው የሴቶችና ወጣቶች፣ ኤች.አይ.ቪ./ኤድስ/ እና ልዩ ፍላጎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር መምህርት ይታገሱ ፍቃዱ በበኩላቸው ዳይሬክቶሬቱ ሴት ተማሪዎች ሊገጥሟቸው ከሚችሉ የተለያዩ ችግሮች ተጠብቀው በትምህርታቸው ውጤታማ መሆን እንዲችሉ የተለያዩ ተግባራትን እንደሚያከናውን ገልፀዋል፡፡

በተለይም ለአዲስ ገቢ ሴት ተማሪዎች ለዩኒቨርሲቲው እንግዳ እንደመሆናቸው መጠን ሊገጥማቸው ከሚችል ችግር እንዲጠበቁ ዳይሬክቶሬቱ ለአዲስ ገቢ ሴት ተማሪዎች በተለየ ትኩረት የተለያዩ ድጋፍና እገዛ ሚያገኙበት ሁኔታዎችን መመቻቸቱን ጠቅሰው ተማሪዎቹም ማንኛው ችግር ሲገጥማቸው ድጋፍ የሚያገኙበት የተለያዩ መልዕከላትን ተከፍተው ለአገልግሎት ክፍት መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡

በዚሁ ስነ-ስርዓት ላይ የድሬደዋ ቤተሰብ መምሪያ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ተወካይ፣ የዩኒቨርሲቲው ሴት መምህራንና የተማሪዎች ህብረት የሴት ተማሪዎች ተወካይ እንዲሁም ባለፈው ወር በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በህግ ትምህርት ቤቶች መካከል በተካሄደው የምስለ ችሎት ውድድር የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲን በመወከል አሸናፊ መሆን የቻሉ ተማሪዎች መልእክት እና ልምዳቸውን አካፍለዋል፡፡

በተጨማሪም የድሬደዋ ቤተሰብ መምሪያና የዩኒቨርሲቲው የሙዙቃና የኪነ-ጥበብ ክበባት የተለያዩ አዝናኝ ዝግጅቶችን በፕሮግራሙ ላይ አቅርበዋል፡፡ 


Share This News

Comment