Logo
News Photo

ሀገር አቀፍ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎች ህብረት ጉባዔ ተካሄደ፡፡

የኢ.ፌደ.ሪ የትምህርት ሚኒስተር  ከድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ እና  ከሃረማያ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር  ባዘጋጀው ጉባዔ ላይ በሀገራችን ከሚገኙ 45 ዩኒቨርሲቲዎች የመጡ የተማሪ ህብረት አመራሮች እና የልዩ ፍላጎት ተወካዮች ተካፋይ ሆነውበታል፡፡ 

በጉበዔው መክፈቻ ላይ የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ የአከዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳነት ዶ/ር መገርሳ ቃሲም በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚገኙ የተማሪ ህብረት አባላት በዩኒቨርሲቲዎች ሰላማዊ የመማርማስተማር ሂደት እንዲኖር የሚጫወቱት ሚና እጅግ የላቀ ነው፡፡

"በተለይም ባለፋት ሁለት ዓመታት በሀገራችን ከፀጥታና ከኮቪድ 19 ወረርሺኝ መከሰት ጋር ተያይዞ ተቋርጦ የነበረውን ትምህርት ዳግም ለማስጀመር በተደረገው ጥረት ውስጥ  የተማሪ ህብረት ፕሬዝዳንቶችና አባላቱ ያበረከቱት አስተዋፆኦ ቀላል ግምት የማይሰጠው ነው" ያሉት ዶ/ር መገርሳ በየከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ የሚገኙ የህብረቱ አመራር ተማሪዎችና አባለቱ ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ በየዩኒቨርሲቲዎች ለተማሪዎች መሰጠት የሚጀምረው የመውጫ ፈተና በሁሉም ተማሪዎች ዘንድ ግንዛቤ እንዲያዝ በማድረግ የበኩል  ጥረት እንዲደርጉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በዚሁ ጉባዔ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት በኢ.ፌ.ደ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር የስኮላርሺፕና አለምአቀፍ ዴስክ ኃላፊ ዶ/ር ኢዶሳ ተርፋሳ በበኩላቸው በየዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የነበሩት ቀደምት የተማሪዎች ህብረት አመራሮች  በየትምህርት ተቋማቸው ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲኖር የተወጡት ሚና በሚኒስቴር መስሪያቤቱ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ነው፡፡ አዲሶቹ የተማሪ ህብረት አመራሮችና አባላቱ ከቀደሙት የህብረቱ አመራሮች ልምድ በመቅሰም በየትምህርት ተቋማቸው ከሚገኙት አማራሮችና ከባለድርሻ አካላት ጋር ተቀራርበው በመስራት ለትምህርት ተቋማቸው ተልዕኮ መሳካት የበኩላቸውን ድርሻ መወጣት ይኖርባቸዋል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በዚህ ጉባዔ ላይ የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደርና የተማሪዎች ጉዳይ ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር አብርሃም አውነቱ ፣በኢ.ፌ.ደ.ሪ የትምህርት ሚኒስቴር የአስተዳደር ጉዳዮች ዴስክ ኃላፊ የተከበሩ አቶ አብዶ ናስር እንዲሁም የቀድሞ እና አዲስ የተማሪዎች ህብረት አመራሮች ልምዳቸውን አካፍለዋል፤ መልእክትም አስተላልፈዋል፡፡

በድሬደዋ ትራያንግል ሆቴል የኢ.ፌደ.ሪ የትምህርት ሚኒስተር  ከድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ እና  ከሃረማያ ዩኒቨርሲቲ ጋር በተባበር  ያዘጋጀው የኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎች  ጉባዔ ከየዩኒቨርሲቲው የተማሪ ህብረቱን እንዲመሩ የተመረጡ የተማሪ ህብረት ፕሬዝዳንቶች እና የልዩ ፍላጎት ተወካዮች ከነባሮቹ የተማሪ አመራሮች ልምድ የሚቀስሙበት ፣የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና የሚሰጥበት እና በቀጣይ አቅጣጫዎች ላይም ውይይት የሚደረግበት መሆኑን ከወጣው መርሀግብር ላይ መረዳት ችለናል፡፡


Share This News

Comment