Logo
News Photo

የምርምር ህትመትና ስርጭትን አስመልክቶ ለድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ስልጠና ተሰጠ።

በዩንቨርሲቲው የምርምር ህትመት፣ ዶክመንቴሽንና ስርጭት ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት በምርምር ህትመትና ስርጭት (Research Publication and Dissemination) ዙሪያ ለሁለት ቀናት የቆየ ስልጠና ተሰጠ፡፡ 

ስልጠናውም ለተመራማሪዎች የሚኖረውን ፋይዳ በተመለከተ የዩኒቨርሲቲው የምርምር ህትመት፣ ዶክመንቴሽንና ስርጭት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ሙሐመድ ቃሶ፣ ይህ ስልጠና በምርምር ህትመትና ስርጭት ዙሪያ  ያለውን ክፍተት የሚሞላና ለቀጣይ ስራም ትልቅ አቅም የሚፈጠር ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ይህንን ስልጠና በንግግር የከፈቱት የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንትና የፕሬዝዳንት ተወካይ የሆኑት ዶ/ር መገርሳ ቃሲም እንዳሉት፣ ከዚህ ቀደም መምህራን በምርምር ስራ ላይ እንዳይሳተፉ  ማነቆ ሆነው የቆዩ ችግሮችን  በመቅረፍ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በዩኒቨርሲቲያችን በርካታ መምህራን በምርምር ስራዎች ላይ  ያላቸውን ተሳትፎ በከፍተኛ መጠን ማሳደግ ተችሏል፡፡  ከቅርብ ቀን በፊት በዩኒቨርሲቲው 50 ያለቁ የምርምር ስራዎች ተዘጋጅቶ የነበረውን የግመገማ  መድረክ ያወሱት ዶ/ር መገርሳ በእንደነዚህ ዓይነት ስልጠናና ድጋፍ የመጣ ውጤት እንደሆናም አንስተዋል፡፡

ስልጠናው ለተመራማሪዎች በቀጣይ ለሚሰሯቸው የጥናትና ምርምር ስራቸውን በተዋቂ ጆርናሎች እንዲያሳትሙና የማህበረሰብን ችግር የሚፈቱ ፕሮጄክቶችንና ንድፈ-ሃሳቦችን እንዲቀርፁ የሚያስችል ግንዛቤና እውቀት እንደሚያገኙ ታሳቢ ተደርጎ የተዘጋጀ ስልጠና በመሆኑ፣ ሰልጠኞቹ በሚያገኑት ግንዛቤ የምርምር ውጤቶቻቸውን በታዋቂ ጆርናሎች ለማሳተምና ለማህበረሰቡ ደርሰው እንዲጠቅሙ ለማድረግ የበኩላቸውን ጥረት ያደርጉ ዘንድ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡

 ለሁለት ቀናት በቆየው በዚህ ስልጠና የሳይንሳዊ ጽሑፎች አፃፃፍ፣ የምርምር ስነ-ምግባር፣ ፣ተዋቂና ተዋቂ ያለሆኑ (ፕሬዳቶሪ) ጆርናሎችን  መለየት፣ኢምፓክት ፋክቶር (Impact Factor)፣በፕሮጄክት አቀራረጽና በሌሎችም ተያያዥነት ባላቸው ርዕሰ-ጉዳዩች ላይ ያጠነጠነ ስልጠና የተሰጠ ሲሆን ስልጠናውም  የኢትዮጵያ ግብርና ኢንስቲዩትና የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር በሆኑት ፕ/ር ንጉሴ ደቻሳ እንዲሁም ከዩንቨርሲቲያችን መምህራን ዶ/ር ሙሐመድ ቃሶና ዶ/ር አዲሱ ጌታቸው የተሰጠ ሲሆን  በስልጠናውም ላይ ከተለያዩ ትምህርት ክፍሎች የተውጣጡ ቁጥራቸው ከ126 በላይ የሆኑ መምህራን መሳተፋቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

 በመጨረሻም በስልጠናው መዝጊያ ላይ  ንግግር ያደረጉት የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ተወካይ  ረ/ፕ ይታገሱ ስንታየሁ ሰልጣኞች ያሰዩትን ትጋት አድንቀው በቀጠይም ዩኒቨርሲቲው የመምህራኑን አቅም ለመገንባት ተከታታይነት ያላቸው ስልጠናዎችን ያዘጋጃል ብለዋል፡፡ 

Share This News

Comment