Logo
News Photo

የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ የመውጫ ፈተናን አስመልክቶ በኮሌጁ ለተቋቋመው ኮሚቴ አባላትና ለኮሌጁ ተማሪዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ፡፡

 የግንዛቤ መስጫ መድረኩን በንግግር የከፈቱት  በዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር መገርሳ ቃሲም እንደገለፁት በሀገራችን ባለፋት ዓመታት የትምህርት ተደራሽነትን ከማስፋት አንፃር የተሰሩት ስራዎች ውጤታማ ቢሆኑም ከጥራት አንፃር ግን ሰፊ ክፍተት መፈጠሩን በተለያዩ ግዚያት የተደረጉ ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡

ይህንን የትምህርት ጥራት ችግር ለመቅረፍም በሀገር አቀፍ ደረጃ የትምህርት ጥራት ፓኬጅን ተግባራዊ በማድረግ የተለያዩ እንቅስቃሴዎች በመደረግ ላይ ነው ያሉት ዶ/ር መገርሳ የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ በሀገራችን በሚገኙ የተለያዩ ከፍተኛ የትምህረት ተቋማት በሚቀጥለው ዓመት ተግባረዊ መደረግ የሚጀምረው የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና የትምህርት ጥራትትን ለማረጋገጥ ከተያዙት ፓኬጆች አንዱና ተጠቃሹ ነው፡፡

በዚህ ረገድም በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ በመጪው 2015 ዓ.ም ለሚጀመረው የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ስኬታማ በሆነ መልኩ መካሄድ እንዲችል ከመምህራንና ጉዳዩ በቀጥታ ከሚመለከታቸው የስራ ኃላፊዎች ብዙ ይጠበቃል ያሉት ዶ/ር መገርሳ    ሰልጣኞች ያገኙትን እውቀት ተጠቅመው ስራቸውን በሙሉ ኃላፊነት ለመወጣት ዝግጁ መሆን ይገባቸዋል ሲሉ አስገንዝበዋል፡፡

በዚሁ መድረክ ላይ በመገኘት ለመምህራኑና ለሚመለከታቸው አካልት ስልጠናውን የሰጡት በዩኒቨርሲቲው የጥራት ማጎልበትና የትምህርት ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ዳንኤል ማሞና የኮሌጁ መምህራኖች  ሲሆኑ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው መምህራኑ የመውጫ ፈተናውን በአግባቡና በተቀመጠው ስታንዳርድ መሠረት መስጠት እንዲችሉና  እንዲሁም ተማሪዎቹ ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ  ብለዋል፡፡

  በሁለት ዙር ተከፍሎ ሲሰጥ በነበረው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ላይ ከቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ተመርጠው በኮሚቴ ውስጥ ለተካተቱ መምህራን እንዲሁም ለኮሌጁ ተማሪዎች ስልጠናው  የተሠጠ መሆኑን ከፕሮግረሙ አስተባባሪዎች መረዳት ችለናል፡፡

Share This News

Comment