Logo
News Photo

የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ሲያስተምራቸው የነበሩ 9 መቶ 97 ተማሪዎች ዛሬ አስመረቀ፡፡

ዩኒቨርሲቲው በዛሬው እለት ያስመረቃቸው ተማሪዎች  በተለያዩ የትምህርት መስኮች ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ 9 መቶ 97 ተማሪዎች ሲሆኑ ተማሪዎቹ  በመደበኛው ፣በማታው ፣ በርቀትና በተከታታይ የትምህርት ክፍለ ጊዜ ትምህርትቸውን ሲከታተሉ ቆይተው ያጠናቀቁ የቅድመ ምረቃና የድህረ ምረቃ ተማሪዎች ናቸው ፡፡ ከተመራቂ ተማሪዎቹ መካከልም 261 ሴት ተማሪዎች መሆናቸው በዚሁ የምረቃ ስነ-ስርዓት ላይ ተገልፃል፡፡

 ለ14ኛ ጊዜ በተዘጋጀው የምረቃ ስነ-ስርዓት ላይ  ለተመራቂ ተማሪዎችና ለተመራቂ ቤተሰቦች እንዲሁም ለመላው የምርቃ ስነ-ስርዓቱ ታዳሚዎች የእንኳን ደስአላችሁ መልዕክት ያስተላለፋት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም ዩኒቨርሲቲው የትምህርት ተደራሽነትን ከማስፋት አንፃር በአሁኑ ሰዓት ቁጥራቸው ከ13 ሺህ በላይ የሚሆኑ ተማሪዎችን በቅድም ምርቃና በድህረ ምረቃ መርሀግብር ተቀብሎ  በማስተማር ላይ መሆኑን ጠቅሰው በበጀት ዓመቱም ተደራሽነቱን በማስፋት በሶማሌ ክልል ሲቲ ዞንና በምስራቅና በምዕራብ  ሐረርጌ ዞኖች በሚገኙ 12  የተለያዩ የወረዳ ከተሞች የሳተላይት ካንፓስ ለመክፈት የዳሰሳ ጥናት በማድረግ ላይ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው  በመማር ማስተማሩ በተለይም የትምህርት ፍትሃዊነትና ጥራትን ከማረጋገጥ አንፃር የመምህራን አቅም ማጎልበትና በተለያዩ ችግሮች ምክንያት ትምህርትቸውን መከታተል ላልቻሉ ነፃ የትምህርት እድልን አመቻችቷል፡፡ እንዲሁም ለሴት ተማሪዎች በተለየ መልኩ ድጋፍና እገዛ እያደረገም ይገኛል፡፡

በጥናትና ምርምሩ ዘርፍም  ለማኅበረሰቡ ችግር ፈቺ የምርምር ስራዎችን ከማበርክት አንፃር  በድሬደዋና በአካባቢዋ አሁናዊ ነባራዊ ሁኔታን መሠረት ያዳረገ የምርምር መስክ ልየታ ስራን በመስራት የተለያዩ ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች መጀመራቸውን ጠቅሰው በዚሁ ዘርፍ በበጀት ዓመቱ 159 የምርምር ስራዎች ማቅረብ ተችሏል፡፡ 

በተጨማሪም አጠቃላይ የመምህራንን በምርምር ስራዎች ላይ ያለቸውን ተሳትፎ 63 በመቶ ማሳደግ የተቻለ ሲሆን የሴት መምህራን  ተሳትፎ ደግሞ 42 በመቶ ማሳደግ መቻሉን ገልፀዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ  በማህበረሰብ አቀፍ አገልልግሎት ዘርፍም ዩኒቨርሲቲው አስገንብቶ ለአየር ላይ ስርጭት ያበቃው የማህበረሰብ ሬድዮ ጣቢያ አንዱና ማህበረሰባችን ጋር በቅርበት ደርስን ችግሩን መፍታት እንድንችል  ትልቅ እድል የሚፈጥርልን ነው ያሉት ዶ/ር ኡባህ የመሠረተ ልማት ከማሻሻል አንፃርም ዩኒቨርሲቲው በ91 ሚሊዮን ብር ያስገነባውና ለተማሪዎች፣ ለመምህርን እና  ለዩኒቨርሲተው ማህበረሰብ ህክምና አገልግሎት  ይሰጣል ተብሎ የተገነባው ዘመናዊ ከፍተኛ ክሊኒክ ከተሰሩት ስራዎች መካከል የተወሰኑትናቸው ብለዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በ2030 በሀገር አቀፍ ደረጃ ተመራጭ ፣በአፍሪካ ደረጃ ተወዳደሪ በአለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ እውቅና ያለው የከፍተኛ የትምህርት ተቋም የመሆን ርዕይውን ለማድረግ የጀመረውን እንቅስቃሴ አጠናክሮ ይቀጥላል ያሉት ዶ/ር ኡባህ ለዚህ ስኬትም ሁሉም ወገን ከጎናችን በመቆም የጀመረውን ድጋፍና ርብርብ አጠናክሮ ይቀጥል በማለት ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡

በዚሁ የምርቃ ስነ-ስርዓት በክብር እንግድነት ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የድሬደዋ አስተዳደር ም/ከንቲባና የአስተዳደሩ የንግድ፣ ኢንደረስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ የተከበሩ አቶ ሃርቢ ቡህ እንዳሉት የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ በድሬደዋ የተጀመረው ፈጣን የልማት እንቅስቃሴ ከዳር እንዲደርስ እያበረከተ ያለው አስተዋፆኦ የአስተዳደሩ መንግስትና ህዝብ ከፍ ያለ ቦታ የሚሰጠው መሆኑን ግልፀው ዩኒቨርሲቲው በቀጥይም የሰለጠነና ብቁ የሰው ኃይል በማፍራት ልማቱን ለመደገፍ ከሚያደርገው ጥረት ጎንለጎን  በጥናትና ምርምር  ችግር ፈቺ ስራዎችን በመስራት እንዲሁም በማህበረሰብ አገልልግት የአስተዳደሩን ነዋሪ ከድህነት ለማላቀቅ በሚደረገው ጥረት የጀመረውን እንቅስቃሴ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡

ተመራቂ ተማሪዎችም ያገኙትን እውቀት ተጠቅመው ለሀገርና ለወግን የሚጠቅም ዜጋ በመሆን በተለይም ሀገር በአሁኑ ሰዓት የተጋረጠባትን ከፍተኛ አደጋ ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት በሚሰለፋበት ግንባር ሁሉ ፊት መሪ በመሆን የተጣለባቸውን የሀገር አደራ መወጣት ይኖርባቸዋል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በምረቃ ስነ- ስርዓቱ ላይ በትምህርታቸው ከፍተኛ ውጤት ማምጣት ለቻሉ የማዕረግና የከፍተኛ ማዕረግ ተማሪዎች የሜዳሊያና የወንጫ ሽልማት ከክብር እንግዶች እጅ ተበርክቶላቸውል፡፡


Share This News

Comment