Logo
News Photo

በዩኒቨርሲቲው የስፓርት ሳይንስ ት/ት ክፍልና ማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ትብብር ሲካሄድ የነበረው በእግርኳስ ስፖርት ፊስቲቫል ውድድር በቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ብድን አሸናፊ በመሆን ተጠናቋል፡፡

የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ የስፖርት ሳይንስ ትምህርት ክፍል ከዩኒቨርሲቲው የማኅበረሰብ አገልግልት ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበር  ካለፈው  ሰኔ 13 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ሲካሄድ የነበረው ዓመታዊ የዩኒቨርሲቲው ሰራተኞች የአግርኳስ ውድድር ዛሬ ፍጻሜውን አግኝቷል፡፡

ፍፃሜውን ባገኘው የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ሰራተኞች ዓመታዊ የእግር ኳስ ውድድር በቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ቡድን አሻናፊነት ሲጠናቀቅ የተፈጥሮ ሳይንስና ኮምፒውቴሽናል ኮሌጅን 4ለ2 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የዋንጫ ባለቤት መሆን ችሏል፡፡

በምድብ 1 የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ፣ የተፈጥሮ ሳይንስና ኮምፒውቴሽናል ኮሌጅ እና የህክምና ሳይንስ ኮሌጅ ቡድኖች የተደለደሉ ሲሆን በምድብ 2 ደግሞ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሲ(C) ፣ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ቢ(B) እና የማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጆች ተደልድልው ላለፋት 24 ቀናት ውድድራቸውን ሲያካሂዱ ቆይተዋል፡፡

በውድድሩም የማህበረሰብ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ ከቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ጋር ለደረጃ ሲገናኙ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሲ(C) እና የተፈጥሮ ሳይንስና ኮምፒውቴሽናል ኮሌጅ ብድኖች ደግሞ ለፍፃሜ ተገናኝተው የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሲ(C) ቡድን የዋንጫ ባለቤት ለመሆን ችሏል፡፡

ጨዋታው በተጀመረ 9ኛው ደቂቃ ላይ በተፈጥሮ ሳይንስና ኮምቲሺናል ኮሌጅ ቡድን የግብ ክልል አቅራቢያ በተፈፀመ ጥፋት የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሲ(C) 12 ቁጥር ለባሹ ሚኪያስ መኮንን የተገኝችውን ፍፁም ቅጣት ምት በግሩም ሁኔታ በማስቆጠር ቡድኑን መሪ ማድረግ ችሏል፡፡በእለቱ ድንቅ ብቃቱን ሲያሳይ የነበረው የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሲ(C) የፊት መስመር ተጨዋቹ ዘይኑ ኡመር በ41ኛውና በ45ኛው ደቂቃ አከታትሎ ሁለት ግቦችን በማስቆጠር የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሲ(C) 3ለ0 በሆነ ውጤት የተፈጥሮ ሳይንስና ኮምፒውቴሽናል ኮሌጅ ክለብን መርቶ እረፍት መውጣት እንዲችል አድርጎታል፡፡

ከእረፍት መልስ ጠንክረው የመጡት የተፈጥሮ ሳይንስና ኮምፒውቴሽናል ኮሌጆች በ66ኛው ደቂቃ ቀዳሚ ግባቸውን ማስቆጠር ቢችሉም በብርሀኑ ተክሉ ከርቀት የተቆጠረችባቸው ድንቅ ጎል ለአቻነት እያደረጉት ያለው ፈጣን ጉዞ አቀዛቅዞባቸዋለች፡፡ ጨዋታው ሊጠናቀቅ 7 ደቂቃ ብቻ ሲቀረው ያገኙትን የፍጽም ቅጣት ምት ቀዳሚዋን ጎል ያስቆጠረው አጥቂው ኃይሌ ለራሱና ለቡድኑ ሁለተኛ ጎል አስቆጥሮ ቡድኑ 4ለ2 እንዲወጣ አድርጎታል፡፡

በዚህ መሰረትም የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሲ(C) ቡድን  የዋንጫ ተሸላሚ መሆን ሲችል ፣ በቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሲ(C) ቡድን 4ለ2 በሆነ ውጤት የተሸነፈው የተፈጥሮ ሳይንስና ኮምፒውቴሽናል ኮሌጅ የብር ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆኗል ፡፡

የማህበረሰብ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ ደግሞ የነሃስ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሲሆን የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ቡድን ደግሞ የፃባይ ዋንጫ ተሸላሚ መሆን  ችሏል፡፡ ዘይኑ ኡመርና ሚኪያስ መኮንን ሁለቱም ከቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሲ(C) ቡድን ኮከብ ግብ አግቢና ኮከብ ተጨዋች ሆነው ተመርጠዋል፡፡

Share This News

Comment