Logo
News Photo

የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በድህረ-ምረቃ ደረጃ ያዘጋጃቸውን የስረዓተ ትምህርቶችን አስገመገመ።

በዚህ የግምገማ መድረክ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር መገርሳ ቃሲም እዳሉት ዩኒቨርሲቲያችን በተልዕኮና በትኩረት መስክ የአፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ እንዲሆን ተወስኖ ይህንኑ ሽግግር ስኬታማ ለማድረግም ሰፊ እንቅስቃሴ እያደረግን እንገኛለን ብለዋል፡፡

በተለይም ዩኒቨርሲቲው በሦስት የትኩረት አቅጣጫዎች (በቢዝንስና ኢኮኖሚክስ ፣በቴክኖሎጂ እና በጤና) አዳዲስ ስርአተ ትምህርት ፕሮግራሞችን በመቅረፅ የተለያዩ እንቅስቃሴዎች በመደረግ ላይ ሲሆኑ የዛሬው መድረክም የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ያዘጋጀው እና ዛሬ ለግምገማ ያቀረበው አዲስ ፕሮግራም የዚሁ እንቅስቃሴ አንድ አካል ነው፡፡

ይህንንም በስኬት በማጠናቀቅ የትምህርት ፕሮግራሞቹን በመክፈት ያሰብነውን ግብ ለመምታት በዚህ የግምገማ መድረክ ላይ ከዩኒቨርሲቲው የተለያዩ ኮሌጆች፣ የትምህርት ክፍሎች እንዲሁም ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የመጡ ምሁራን ተጋባዝ የሆናችሁ ምሁራን የበኩላቸሁን አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ ዶ/ር መገርሳ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

በዩኒቨርሲቲው የትምህርት ጥራት ማሻሻልና መርሃ-ግብር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ዳንዔል ማሞ በበኩላቸው በዛሬው የግምገማ መድረክ ላይ ቁጥራቸው 4 የሆኑ በድህረ ምረቃ ደረጃ ያሉ የስረዓተ ትምህርት ፕሮግራሞች (MPH in Reproductive HEALTH, MPH inEpidemiology , MSC in Maternity Nursing and MSC in Medical Micro Biology)  ቀርበው ግምገማ የተደረገባቸው ሲሆን በቀጣይም በባለሞያ የሚሰጡትን አስተያየት አካትተው ለሴኔት ቀርበው ከፀደቁ ቦኋላ የሚከፈቱ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

Share This News

Comment