Logo
News Photo

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ውይይት በድሬደዋ ዩኒቨርሲተ

በድሬደዋ ዩኒቨርሲተ አዘጋጅነት የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሁለታ ዙር የውኃ ሙሌት መጣናቀቅን አስምልክቶ የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ዛሬ ማለዳ ላይ የጀመረውና በድሬደዋ አስተዳደር የምክርቤት አዳራሽ እየተካሄደ የሚገኘው የፓናል ውይይት 2ኛው ዙር የኢትዮጵያ የህዳሴው የውኃ ሙሌትን መጠናቀቅ አስመልክቶ እየተካሄደ የሚገኝ ሲሆን በዚህ የፓናል ውይይት ላይም የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ድኤታ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ ፣ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ማስተባበሪያ ብሄራዊ ምክር ቤት ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር አረጋዊ በርሄ፣ የድሬደዋ አስተዳደር ከንቲባ መሐመድ አህመድ ቡህ ፣ የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ኡባህ አደም ጨምሮ የአገራችን ከፍተኛ ባለስልጣናት እና የተለያዩ የዩኒቨርሲቲ ምሁራን እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳታፊ መሆናቸውን ታውቋል፡፡
ይህ የፓናል ውይይት ለአንድ ቀን የሚቆይ ሲሆን በዛሬው የከሰዓት ውሎም የተለያዩ ጥናታዎ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል ተብሎ ይጠበቀል፡፡

Share This News

Comment