Logo
News Photo

አዲሱ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ቦርድ በይፋ ስራውን ጀመረ፡፡

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ፍፁም አሰፋ ሰብሳቢነት የሚመራው አዲሱ ቦርድ ከቀድሞው ቦርድ ሙሉ ኃላፊነቱን ተረክቦ በይፋ በትላንትናው እለት ስራውን የጀመረ ሲሆን በውሎውም የ2014 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ገምግሞ ያፀደቀ ሲሆን የ2015 ዓ.ም እቅድ ላይ ተወያይቶ ማፅደቅ ተችሏል።

በዛሬው ውሎ በዩኒቨርሲቲው በመገኘት እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን የቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት ክብርት ዶ/ር ፍፁም አሰፋ በጉብኝቱ ወቅት እንደገለፁት ዩኒቨርሲቲው በመማር ማስተማር ፣ በጥናትና ምርምር እና በማኅበረሰብ አቀፍ አገልግልት እያከናወናቸው ያሉት ተግባራት የሰነቀውን ርዕይ እውን ከማድረግ አንፀር እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ የሚበረታታና ተጠናክሮ መቀጠል የሚገባው ነው ብለዋል።

ዩኒቨርሲቲው በተለይም  የመማር ማስተማር ሂደቱን  በዲጂታል ቴክኖሎጂ ለተማሪው ተደራሽ ለማድረግ ዘመናዊ የዳታ ሴንተር በማቋቋም የሄደበት ርቀት እጅግ የሚደነቅና ለሌሎች መሰል ተቋማትም አርያ የሚሆን ተግባር ነው ብለዋል፡፡ቦርዱ በቀጣይ ትኩሩት የሚሹ ስራዎች ላይ አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡

የአዲሱ የቦርድ አባላት በዩኒቨርሲቲው ግንባታቸው በመጠናቀቅ ላይ የሚገኙትን ግዙፍ ቤተ-መጽሐፍ ፣ ዘመናዊ ከፍተኛ ክሊኒክ እንዲሁም የመረጃና መገናኛ ቴክኖሎጂ የስራ እንቅስቃሴ፣ የሙከራ ስርጭቱን የጀመረውን የዩኒቨርሲቲውን ማህበረሰብ ሬድዮ ጣቢያ ፣የተለያዩ ላብራቶሪዎች እና የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ እያስገነባው ያለውን የድሬደዋ ሪፈራል ቲቺንግ  ሆስፒታል ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን በአረንጓዴ አሻራ መርሀግብርም በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ውስጥ የችግኝ ተከላ አካሂደዋል፡፡


Share This News

Comment