Logo
News Photo

የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ 4ኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብርን በማስመልክት የተለያዩ ሀገር በቀል ችግኞችን ለኅብረተሰቡ አከፋፈለ፡፡

የድሬ ዳዋ ዩኒቨርሲቲ 4ኛውን ዙር ሃገራዊ የአረንጓዴ አሻራ ማኖር መርሃ-ግብርን በማስመልከት ከሃምሌ 16/2014 ዓ/ም ጀምሮ የችግኝ ተከላ ፕሮግራሞችን እያከናወነ  ይገኛል፡፡ የዚሁ የአረንጓዴ አሻራ ማኖር አካል የሆነ ዩኒቨርሲቲው በራሱ ባቋቋመው የችግኝ ማፍያ ማዕከል ያፈላቸውን የተለያዩ ሀገር-በቀል የጥላ ዛፍ ችግኞችን በሰኢዶና፤ ጎሮና፤ አካባቢው ለሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች እያከፋፈለ ይገኛል፡፡ 

ችግኝ በማከፋፈሉ ፕሮግራም ላይ የተገኙት በዩኒቨርሲቲው የማኅበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ወንዲፍራው ደጀኔ እንዳሉት በዘንድሮው ዓመት የተቋቋመው ችግኝ ማፍያ ማዕከል የዩኒቨርሲቲውን የችግኝ ፍላጎት ከማሟላት አልፎ ለአካባቢው ማኅበረሰብ መትረፉ አረንጓዴ ኢኮኖሚ ለመገንባት የሚደረገውን ጥረት ለመደገፍ ዩኒቨርሲቲው የራሱን አስተዋፆ እያበረከተ መሆኑን ያሳያል ብለዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው የችግኝ ማፍያ ማዕከል አስተባባሪ  የሆኑት መምህር ታምራት መገርሳ በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው አዲስ ባቋቋመው የችግኝ ማፍያ ማዕከል ውስጥ በአሁኑ ሰዓት የተለያዩ ሀገር በቀል ችግኞችን እያፈላ መሆኑን ጠቅሰው በያዝነው በጀት ዓመት ከጥላ ዛፎች በተጨማሪ ለምግብነት የሚሆኑ የፍራፍሬ ችግኞችን በማፍላት የአካባቢውን ማህበረሰብ ይበልጥ ተጠቃሚ ለማድረግ ዕቅድ ይዞ እየተንቀሳቀሰ ነው ብለዋል፡፡


Share This News

Comment