Logo
News Photo

በሀገራችን አዲስ የተከሰተችውን አኖፕለስ ስቴፈንሲ የተሰኘች የወባ በሽታን አምጪ ትንኝ መከላከል የሚያስችል ፕሮጀክት ማስጀመሪያ ፕሮግራም ዛሬ በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ተካሄደ፡፡

አኖፕለስ ስቴፈንሲ (Anopheles Stephensi) የተሰኘችው የወባ በሽታ አምጪ ትንኝ በቅርቡ በአስተዳደራችችን ድሬደዋን ጨምሮ በሶማሌ ፣ በአፋር እና በተወሰኑ የኦሮምያ ክልል ከተሞች መከሰቷ ተረጋግጧል፡፡

ይህቺን በሀገራችን እንደ አዲስ የተከሰተች የወባ በሽታን አምጪ ትንኝ በማኅበረሰቡ ላይ ጉዳት ከማድረሷ በፊት አስቀድሞ ለመከላከል በአሜሪካ መንግስት ( U.S. President's Malaria Initiative vectorlink Ethiopia) በተደረገ የገንዘብ ድጋፍ  የተለያዩ ባለድርሻ አካላት የታቀፉበት ፕሮጀክት በዛሬው እለት በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ በይፋ የፖሮጀክቱ ማስጀመሪያ ፕሮግራም ተካሂዷል፡፡

በዚሁ የፕሮጀክት ማስጀመሪያ ፕሮግራም ላይ የድሬደዋ አስተዳደር ከንቲባ የተከበሩ አቶ ከድር ጁሀር ፣ የድሬደዋ የብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ ዘር ኃላፊ የተከበሩ አቶ ኢብራሒም ዩሱፍ ፣ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኢንባሲ ትሬሲ ጃኮብሰን ፣ የድሬደዋ አስተዳዳር ጤና ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ለምለም በዛብህ ፣ ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጤና  ሚኒስቴር የተለያዩ የሥራ ክፍል ኃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡   

ይህንኑ የፖሮጀክት ማብሰሪ ፕሮግራም በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር የከፈቱት የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም ዩኒቨርሲቲው በምስራቁ አካባቢ ያለው የጤና አገልግልት እንዲሻሻል የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ላይ መሆኑን ጠቅሰው በተለይም በህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጁ በቅርቡ በድሬደዋና በአካባቢው እንደተከሰተች የተረጋገጠውን አኖፕለስ ስቴፈንሲ (Anopheles Stephensi) የተሰኘችውን የወባ በሽታን አምጪ ትንኝ በማኅበረሰባች ላይ ጉዳት ከማድረሷ በፊት አስቀድሞ ለመከላከል ዛሬ በይፋ የተጀመረው ፕሮጀክት ስኬታማ እንዲሆን በቂ ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱን ተናግረዋል፡፡

በትንኝ ንክሻ የሚተላለፉ በሽታዎች የአስተዳደራችንን ዋነኛ የማኅበረሰባችን የጤና ችግሮች መሆኑን የገለጹት  የድሬደዋ አስተዳደር ከንቲባ የተከበሩ አቶ ከድር ጁሀር  እነዚህን በሽቶች ለመከላከልና ለመቆጣጠር በርካታ ተግባራት በመከናወን ላይ እንደሚገኙ ጠቅሰው በተለይም የአስተዳደሩ ከፍተኛ የካቢኔ አባላትና ከፍተኛ አመራሮች የሚሳተፉበት የእለተ ቅዳሜ የፅዳት ፕሮግራም ለውጥ እያመጣ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

እንደ ሀገርም ሆነ እንደ አስተዳዳር በዚህ ፕሮጀክት ላይ በቀጥታ ተሳትፎ ያላቸው የአሜሪካ መንግስት፣ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የጤና ሚኒስቴር፣ የድሬደዋ ጤና ቢሮ እና የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ትንኟን ለመከላከል የተከተሉት አዲስ ስልት ሊበረታታ የሚገባውና ሊያስመሰግናቸው የሚገባ ነው ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኢንባሲ ትሬሲ ጃኮብሰን በበኩላቸው ኢትዮጵያ ወባን ለማጥፋት የምታደርገውን እንቅስቃሴ አሜሪካ ድጋፏን አጠናክራ ትቀጥላለች ፡፡ በተለይ በአዲስ መልክ በኢትዮጵያ የተለያዩ የክልል ከተሞች የተከሰተችውን አኖፕለስ ስቴፈንሲ የተሰኘችውን የወባ በሽታ አምጪ ለማጥፋት ለሚደረገው ጥረት ድጋፉ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

የድሬደዋ አስተዳዳር ጤና ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ለምለም በዛብህ በዚሁ ወቅት እንዳሉት ካለፈው ዓመት ወዲ በአስተዳደሩ በትንኝ ንክሻ አማካኝነት ከወባ በሽታ በተጨማሪ የደንጊ ትኩሳትና የቺኩንጉኒያ በሽታዎች በማኅበረሰባች ላይ ከፍተኛ የጤና ችግር እያስከተሉ እንደሚገኙ ጠቅሰው በተለይ ካለፈው ዓመት ወዲህ የነዚ ወረርሽኝ ሽረጭት መጨመር ተከትሎ ከዚህ ቀደም የወባ በሽታን በመከላከል ረገድ ያስመዘገብነው ውጤትን በዘላቂነት ማስቀጠል እንዳንችል ከባድ ፈተና እየፈጠረብን በመሆኑ ሁላችንም ተረባርብን ፖሮጀክቱን ስኬታማ ማድረግ ይጠበቅብናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

አንደ ድሬደዋም የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ ፣ የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ እንዲሁም ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በመሆን በዛሬው እልት የፕሮጀክት መጀመር ማብሰሪያ ፕሮግራም መካሄዱ ተነግሯል፡፡


Share This News

Comment