Logo
News Photo

የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ካውንስል በ2014 በጀት አመት የእቅድ አፈፃፀም እና የ2015 በጀት አመት እቅድ ላይ ውይይት አካሄደ፡፡

ዩኒቨርሲቲው በተጠናቀቀው በጀት አመት በተቀመጡት ስትራቴጂክ ግቦች፣ የፕሮጀክት አፈፃፀም ፣ በበጀት አመቱ ባጋጠሙ ችግሮች እና በቀጣይ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ላይ ውይይት ያደረገ ሲሆን በበጀት ዓመቱ በመማር ማስተማሩ ዘርፍ ዩኒቨርሲቲውን ወደ አፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲነት ለማሻገር የሚያስችሉ ስራዎች መጀመራቸው እና የትምህርት ጥራትን ከማስጠበቅ አንፃር በ2015 ዓ.ም ለመጨረሻ ዓመት ተማሪዎች ሊሰጥ የታቀደው የመውጫ ፈተናን አስመልክቶ ዝግጅት መጀመሩን በሪፖርቱ ላይ ተገልጿል፡፡

በተመሳሳይም በምርምርና ማኅበረሰብ አገልግልት በበጀት ዓመቱ በርካታ ውጤታማ ስራዎች የተሰሩ መሆናቸውን፣ በመሠረተ ልማት ማሳፋፋት ስራዎች ዘርፍም በበጀት ዓመቱ የተለያዩ የግንባታ ፕሮጀክቶች ክንውናቸው በሪፖርት ላይ ተገልጿል፡፡

በግምገማዊ መድረኩ ዩኒቨርሲቲው በ2014 ዓ.ም በመማር ማስተማር፣ በምርምርና ማኅበረሰብ አገልግልት እንዲሁም በመሠረተ ልማት ግንባታ እና ማስፋፊያ ስራዎች ላይ ከእቅዱ አንፃር በበጀት ዓመቱ የነበረው አፈፃፀም በዝርዝር ቀርቦ በተሳታፊዎች ውይይት ተደርጎበታል፡፡

በመድረኩ ላይ ተሳታፊ የነበሩት የዩኒቨርሰቲ ካውንስል አባላት በቀረበው ሪፖርት ላይ የተለያዩ ጥያቄዎችን እና አስተያየቶችን በማቅረብ ውይይት በማድረግ ዩኒቨርሲቲው በ2015 በጀት ዓመት ሪዕይና ተልዕኮውን እንዲሳካ እና የተጀመሩት የለውጥ ስራዎች ከግብ እንዲደርሱ ማህበረሰቡ ሁሉም በየ ደረጃው ለእቅዱ ተፈፃሚነት ሀላፊነቱን እና ግዴታው በተሻለ ሁኔታ እንዲወጣ የዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም በንግግራቸው አሳስበዋል።

Share This News

Comment