Logo
News Photo

የመሰናዶ ትምህርታቸውን ላጠናቀቁ ተማሪዎች የሚሰጠውን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና አስመልክቶ በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ውይይት ተካሄደ፡፡

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2014 ዓ/ም ትምህርት ዘመን የሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ፈተና በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እንዲሰጥ በተቀመጠ አቅጣጫ መሠረት የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በ2014 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና በተያዘለት ፕሮግራም ለማከናወን የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ላይ  በዩኒቨርሲቲው ከተቋቋመው ግብረሀይል ጋር ውይይት ተደርጓል።

የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ውይይት የተደረገ ሲሆን የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር መገርሳ ቃሲም በዚሁ መድረክ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ላይ እንዳመለከቱት ዩኒቨርሲቲው የተጣለበትን ሀገራዊ የማጠቃለያ ፈተናውን በስኬት ለመፈፀም ሁሉም አካል የተጣለበትን ሃላፊነት በከፍተኛ ትኩረት ማከናወን እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

ዶ/ር መገርሳ አክለውም የሚያስፈልጉ አገልግሎቶች ሙሉ በሙሉ ዝግጁ በማድረግ በኩል ሁሉም የኮሜቴው አባላት በሙሉ ሃላፊነት በመረባረብ ስራውን በአጭር ጊዜ ውስጥ ማጠናቀቅ ይኖርባቸዋል ሲሉ አሳስበዋል፡፡

የአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶ/ር አብረሃም እውነቱ በበኩላቸው እንደገለፁት የግብረ ኃይሉ አባለት ተግባርና ኃላፊነታቸውን አውቀው ለውጤታማነቱ በትጋት መስራት ይኖርበታል ብለዋል፡፡ 

በመጨረሻም የማጠቃለያ ፈተናውን ስኬታማ በሆነ መንገድ ማጠናቀቅ በሚያስችል ሁኔታዎች ላይ ከተሳታፊዎች ጋር ውይይት ተደርጎበታል።

Share This News

Comment